ስጋዊ ሞት
የሰውነት ከመንፈስ መለየት። ውድቀት ሟችነትንና በምድርም ሞትን አመጣ (፪ ኔፊ ፪፥፳፪፤ ሙሴ ፮፥፵፰)። የኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ ሁሉም ሰው ከሞት እንዲነሱ ዘንድ ሞትን አሸነፈ (፩ ቆሮ. ፲፭፥፳፩–፳፫)። ትንሳኤ በዚህ ህይወት ጥሩ ወይም መጥፎ ቢያደርጉም ለሁሉም ሰዎች የተሰጠ የነጻ ስጦታ ነው (አልማ ፲፩፥፵፪–፵፬)። ከሞት ከተነሳን በኋላ ሰውነቶቻችን እንደገና መሞት ስለማይችሉ፣ እያንዳንዱ ሰው ስጋዊ ሞት የሚኖረው አንዴ ብቻ ነው (አልማ ፲፩፥፵፭)።