መፅሐፈ ትእዛዛት ደግሞም ራዕይ; ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ተመልከቱ በ፲፰፻፴፫ (እ.አ.አ.)፣ ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ የተቀበላቸው ብዙ ራዕያት A Book of Commandments for the Government of the Church of Christ በሚል በተሰጠር ርዕስ ለህተማ ተዘጋጅተው ነበር። ጌታ ከአገልጋዮቹ ጋር መነጋገሩን ቀጥሏል፣ እና ከሁለት አመት በኋላ የተስፋፉ የራዕዮች ጥርዝ እንድ ት. እና ቃ. ታተመ። ት. እና ቃ. ፩ ለመፅሐፈ ትእዛዛቱ መቅድም የሰጠው ነው, ት. እና ቃ. ፩፥፮. ጌታ ጥበባዊ ሰውን በመፅሐፈ ትእዛዛቱ ውስጥ ያለውን ታናሽኘውን ራዕዩን አመሳስሎ ለመጻፍ የሚችል እንዳለ ጠየቀ, ት. እና ቃ. ፷፯፥፬–፱. እነዚህን ራዕያት እንዲያትሙ መጋቢዎች ተመድበው ነበር, ት. እና ቃ. ፸፥፩–፭.