ቃየን ደግሞም አቤል; አዳም; የሚስጥር ስብሰባ; ግድያ ተመልከቱ ታናሽ ወንድሙን አቤልን የገደለው የአዳም እና የሔዋን ወንድ ልጅ (ዘፍጥ. ፬፥፩–፲፮)። መስዋዕቱ በጌታ ተቀባይነትን አላገኘም, ዘፍጥ. ፬፥፫–፯ (ሙሴ ፭፥፭–፰፣ ፲፰–፳፮). ወንድሙን አቤልን ገደለ, ዘፍጥ. ፬፥፰–፲፬ (ሙሴ ፭፥፴፪–፴፯). ጌታ ረገመው እናም ምልክት አደረገበት, ዘፍጥ. ፬፥፲፭ (ሙሴ ፭፥፴፯–፵፩). አዳምና ሔዋን እርሱ ከመወለዱ በፊት ብዙ ወንድ እና ሴት ልጆች ወለዱ, ሙሴ ፭፥፩–፫፣ ፲፮–፲፯. ሰይጣንን ከእግዚአብሔር በላይ ወደደ, ሙሴ ፭፥፲፫፣ ፲፰. ከሰይጣን ጋር ቅዱስ ያልሆነ ቃል ኪዳን ገባ, ሙሴ ፭፥፳፱–፴፩.