የጥናት እርዳታዎች
መለወጥ


መለወጥ

የሰማይ ሰዎችን ለማየትና ክብራቸውን ለመቋቋም እንዲችሉ ዘንድ ሰዎች በፍጥረት እና በአመለካከት ለጊዜአዊ የሚቀየሩበት ሁኔታ—ይህም ማለት፣ ወደ ከፍተኛ መንፈሳዊ ደረጃ ከፍ ተደርገዋል ማለት ነው።

የክርስቶስ መለወጥ

ጴጥሮስ፣ ያዕቆብ፣ እና ዮሐንስ በፊት ለፊታቸው ግርማዊና የተለወጠውን ጌታ አዩ። አዳኝ ከእዚህ በፊት ለጴጥሮስ የመንግስተ ሰማይ ቁልፎችን እንደሚቀበል ቃል ገብቶለት ነበር (ማቴ. ፲፮፥፲፫–፲፱፲፯፥፩–፱ማር. ፱፥፪–፲ሉቃ. ፱፥፳፰–፴፮፪ ጴጥ. ፩፥፲፮–፲፰)። በዚህ አስፈላጊ ድርጊት፣ አዳኝ፣ ሙሴ፣ እና ኢልያ (ኤልያስ) ቃል የተገቡትን የክህነት ቁልፎች ለጴጥሮስ፣ ያዕቆብ፣ እና ዮሐንስ ሰጡ። በእነዚህ የክህነት ቁልፎች፣ ሐዋሪያት ኢየሱስ ካረገ በኋላ የመንግስትን ስራ ለመቀጠል ሀይል ነበራቸው።

በመለወጫ ተራራ ላይ ጴጥሮስ፣ ያዕቆብ፣ እና ዮሐንስ ተለውጠው እንደነበር ጆሴፍ ስሚዝ አስተምሯል። እነርሱም ምድርን ወደፊት በተከበረችበት ሁኔታዋ የምትመስልበትን ራዕይ አዩ (ት. እና ቃ. ፷፫፥፳–፳፩)። እነርሱም የተቀየሩትን ሙሴን እና ኤልያስን አዩ እናም የአብን ድምፅ ሰሙ። አብም እንዲህ አለ፣ “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው” (ማቴ. ፲፯፥፭)።

የተለወጡ ሰዎች