ጌታ ደግሞም ኢየሱስ ክርስቶስ; እግዚአብሔር፣ አምላክ ተመልከቱ ለአብ እግዚአብሔርና ለአዳኝ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚሰጥ ጥልቅ ርዕስ። ርዕሱም በፈጠሩት ላይ ስላላቸው ታላቅ፣ አፍቃሪ አዛዥነት ሁኔታ የሚጠቁም ነው። በውኑ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለም, ዘፍጥ. ፲፰፥፲፬. እግዚአብሔርም ፊት ለፊት ከሙሴ ጋር ተነጋገረ, ዘፀአ. ፴፫፥፲፩. አንተም አምላክህን እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ ውደድ, ዘዳግ. ፮፥፭ (ማቴ. ፳፪፥፴፯; ማር. ፲፪፥፴). እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን, ኢያ. ፳፬፥፲፭. እግዚአብሔር እረኛዬ ነው, መዝ. ፳፫፥፩. እግዚአብሔር ብርቱና ኃያል፣ በሰልፍ ኃያል ነው, መዝ. ፳፬፥፰. ጌታ እግዚአብሔር ኃይሌ ነው, ኢሳ. ፲፪፥፪ (፪ ኔፊ ፳፪፥፪). እኔም እግዚአብሔር መድኃኒትሽና ታዳጊሽ ነኝ, ኢሳ. ፷፥፲፮. ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ, ማቴ. ፬፥፲ (ሉቃ. ፬፥፰). ጌታ እንዴት ያለ ታላቅ ነገር አደረገልህ, ማር. ፭፥፲፱. አንድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አለን, ፩ ቆሮ. ፰፥፮. አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት, ኤፌ. ፬፥፭. ጌታ ራሱ ከሰማይ ይወርዳል, ፩ ተሰ. ፬፥፲፮. እኔ ጌታ ያዘዘኝንም ነገሮች አደርጋለሁ, ፩ ኔፊ ፫፥፯. ጌታ እግዚአብሔር ድሆችን በፅድቅ ይፈርዳል, ፪ ኔፊ ፴፥፱. ጌታ እግዚአብሔር፣ የአብርሃም አምላክ፣ እስራኤላውያንን ከባርነት ለቋቸዋል, አልማ ፳፱፥፲፩. በጌታ እምነት ካልሆነ በቀር ይህን ህዝብ ምንም ሊያድን አይችልም, ሔለ. ፲፫፥፮ (ሞዛያ ፫፥፲፪). የጌታህን እና የኢየሱስ ክርስቶስን ቃላት አድምጥ, ት. እና ቃ. ፲፭፥፩. የጌታን ፊት ሁልጊዜም እሹ, ት. እና ቃ. ፻፩፥፴፰. ጌታም በዳግም ምፅዓት በልብሱ ቀይ ይሆናል, ት. እና ቃ. ፻፴፫፥፵፰ (ኢሳ. ፷፫፥፩–፬). አብርሐም ከጌታ ጋር ፊት ለፊት ተነጋገረ, አብር. ፫፥፲፩. ፬ የወንጌሉ ቀዳሚ መሰረቶችና ስነስርዓቶች፥ አንደኛ፣ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እምነት…እንደሆነ እናምናለን, እ.አ. ፩፥፬.