የጥናት እርዳታዎች
ወደ ገላትያ መልእክት


ወደ ገላትያ መልእክት

በአዲስ ኪዳን ውስጥ ያለ መፅሐፍ። በገላትያ ውስጥ ለሚኖሩት ቅዱሳን ሐዋሪያው ጳውሎስ የጻፈው ደብዳቤ ነበር። የዚህ ደብዳቤ ጭብጥ መልእክት እውነተኛ ነጻነት ለመገኘት የሚቻለው በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል በመኖር ነው የሚል ነበር። ቅዱሳን የሙሴን ህግ መከተል አለባቸው የሚሉት የአይሁዳ ክርስቲያን ትምህርቶችን ከወሰዱ፣ በክርስቶስ ያገኙትን ነጻነት ይገድባሉ ወይም ያጠፋሉ። መልእክቱ ውስጥ ጳውሎስ የሐዋሪያ ሀላፊነቱን አረጋገጠ፣ የጽድቅ በእምነት ትምህርትን ገለጸ፣ እናም የመንፈሳዊ ሀይማኖት ታላቅ ዋጋን አረጋገጠ።

በምዕራፍ ፩ እና ፪፣ ጳውሎስ በገላትያ መካከል ስላለው ክህደት በተቀበለው ዜና ሀዘኑን ገለጸ እናም በሐዋሪያት መካከል ስላለው ቦታ ገለጸ። ምዕራፍ ፫ እና ፬ የእምነትና የስራ ትምህርቶችን ይወያያሉ። ምዕራፍ ፭ እና ፮ የእምነት ትምህርት ውጤቶች ስብከትን የያዙ ናቸው።