ሳንሀድሪን ደግሞም አይሁዶች ተመልከቱ የአይሁድ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት እና በህዝባዊ እና በሀይማኖታዊ ነገሮች ውስጥ የአይሁድ ታላቅ ፍርድ ቤት። ሳንሀድሪን ከዋና ካህናት፣ ጸሀፊዎች፣ እና ሽማግሌዎች መካከል የተመረጡ ሰባ አንድ አባላት ያለው ነው። በቅዱሣት መጻህፍት ውስጥ፣ ይህም ሽንጎ ተብሎ ይጠራል (ማቴ. ፳፮፥፶፱፤ ማር. ፲፬፥፶፭፤ የሐዋ. ፭፥፴፬)።