መንግስት ደግሞም ህገ መንግስት ተመልከቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲመለስ፣ የጻድቅ መንግስት ይመሰርታል። አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል, ኢሳ. ፱፥፮ (፪ ኔፊ ፲፱፥፮). እንኪያስ የቄሣርን ለቄሣር አስረክቡ, ማቴ. ፳፪፥፳፩ (ት. እና ቃ. ፷፫፥፳፮). ለባለ ሥልጣኖች ይገዛ, ሮሜ ፲፫፥፩. ለነገሥታትና ለመኳንንትም ሁሉ ጸልይ, ፩ ጢሞ. ፪፥፩–፪. ለገዦችና ለባለ ሥልጣኖች የሚገዙና የሚታዘዙ ሁኑ, ቲቶ ፫፥፩. ስለ ጌታ ብላችሁ ለሰው ሥርዓት ሁሉ ተገዙ, ፩ ጴጥ. ፪፥፲፫–፲፬. የዓለም መንግሥት የክርስቶስ ትሆናለች, ራዕ. ፲፩፥፲፭. ፃድቅ ሰው የእናንተ ንጉስ ይሁን, ሞዛያ ፳፫፥፰. በህዝቡም ድምፅ ጉዳያችሁን ፈፅሙ, ሞዛያ ፳፱፥፳፮. ክርስቶስ በሚመጣበት ጊዜ የእኛ ገዢ ይሆናል, ት. እና ቃ. ፵፩፥፬. የእግዚአብሔርን ህግጋትን የሚጠብቅ የምድርን ህግጋት የመጣስ ፍላጎት አይኖረውም, ት. እና ቃ. ፶፰፥፳፩. ክፉው ሲያስተዳድር ህዝቡ ያዝናል, ት. እና ቃ. ፺፰፥፱–፲. መንግስቶች እግዚአብሔር ለሰው ጥቅም የመሰረታቸው ናቸው, ት. እና ቃ. ፻፴፬፥፩–፭. ሰዎች መንግስቶች ለመቀበል እና ለመደገፍ ግዴታ አላቸው, ት. እና ቃ. ፻፴፬፥፭. ፲፪ ለንጉሶች፣ ለፕሬዘደንቶች፣ ለመሪዎች፣ እናም ለዳኛዎች ታዛዦች በመሆን፣ በህግ በመታዘዝ፣ በማክበርና በመደገፍ እናምናለን, እ.አ. ፩፥፲፪.