የክህነት ቁልፎች
ቁልፎች የአመራር መብቶች፣ ወይም የእግዚአብሔርን ክህነት በምድር ላይ እንዲመራ፣ እንዲቆጣጠር፣ እና ገዢ እንዲሆን በእግዚአብሔር ለሰው የተሰጠ ሀይል ነው። ለአመራር ኃላፊነት የተጠሩ የክህነት ባለስልጣኖች ቁልፎችን ከእነርሱ በላይ ስልጣን ካላቸው ይቀበላሉ። የክህነት ባለስልጣኖች ክህነትን ለመጠቀም የሚችሉት ቁልፎችን የያዙት በሚሰጡት መጠን ውስጥ ብቻ ነው። የቤተክርስቲያኗ ፕሬዘደንት በምድር ላይ ሁሉንም የክህነት ቁልፎች ለመያዝና ለመጠቀ የሚችለው የቤተክርስቲያኗ ፕሬዘደንት ብቻ ነው (ት. እና ቃ. ፻፯፥፷፭–፷፯፣ ፺፩–፺፪፤ ፻፴፪፥፯)።