ምሳሌ መንፈሳዊ እውነት ወይም መሰረታዊ መመሪያ ለማሳየት እና ለማስተማር የሚጠቀሙበት ታሪክ። ምሳሌ ልዩ ያልሆነ ነገርን ወይም የእውነት ድርጊቶችን በማነጻጸር ላይ የተመሰረተ ነው፣ እናም የምሳሌ ዋና መልእክት ይህን ለመቀበል በመንፈስ ላልተዘጋጁት አዳማጮች የተደበቀ ነው (ማቴ. ፲፫፥፲–፲፯)። ኢየሱስ ክርስቶስ ብዙ ጊዜ በምሳሌዎች አስተማረ። የወንጌሎች ስምምነትን በተጨማሪ ውስጥ ተመልከቱ።