የጥናት እርዳታዎች
መንፈስ


መንፈስ

ከምድራዊ ውልደት በፊት የነበረው፣ በስጋዊ ሰውነት ውስጥ በምድራዊ ህይወት ጊዜ የሚኖር፣ እናም ከሞት በኋላም እስከ ትንሳኤ ድረስ ተለይቶ የሚኖረው የህያው ሰው ክፍል። ሁሉም ህያው ነገሮች፣ የሰው ዘር፣ እንስሳት፣ እና ተክል፣ በምድር ላይ ምንም አይነት ህይወት ከመኖሩ በፊት መንፈሶች ነበሩ (ዘፍጥ. ፪፥፬–፭ሙሴ ፫፥፬–፯)። የመንፈስ ሰውነት ከስጋ ሰውነት ጋር አንድ ይመስላሉ (፩ ኔፊ ፲፩፥፲፩ኤተር ፫፥፲፭–፲፮ት. እና ቃ. ፸፯፥፪፻፳፱)። መንፈስ ንጥረ ነገር ነው፣ ነገር ግን ከምንም ንጥረ ነገር በላይ የጠራ እና ንጹህ ነው (ት. እና ቃ. ፻፴፩፥፯)።

በምድር ላይ ወደ ሟች ወላጆች ከመወለዳቸው በፊት ለሰማይ ወላጆች እንደ መንፈስ የተወለደው እያንዳንዱ ሰው የእግዚአብሔር ወንድ ወይም ልጅ ነው (ዕብ. ፲፪፥፱)። በምድር ላይ ያለ እያንዳንዱ ሰው ከስጋ እና አጥንት ሰውነት በተጨማሪ የማይሞት የመንፈስ ሰውነት አለው። በቅዱሣት መጻህፍት ውስጥ አንዳንዴ ትርጉም እንደሚሰጣቸው፣ መንፈስ እና ስጋዊ ሰውነት በአንድነት ነፍስን ይሰራሉ (ዘፍጥ. ፪፥፯ት. እና ቃ. ፹፰፥፲፭ሙሴ ፫፥፯፣ ፱፣ ፲፱አብር. ፭፥፯)። መንፈስ ያለስጋዊ ሰውነት ለመኖር ይችላል፣ ነገር ግን ስጋዊ ሰውነት ያለመንፈስ ለመኖር አይችልም (ያዕ. ፪፥፳፮)። ስጋዊ ሞት የመንፈስ ከሰውነት መለየት ነው። በትንሳኤ ጊዜ፣ ከሁለት ታላቅ ልዩ ጋር፣ መንፈስ በሟችነት እንደነበረው ምድራዊ የስጋ እና የአጥንት ሰውነት ጋር እንደገና አንድ ይሆናል፥ ሁለቱም እንደገና አይለያዩም፣ እና ስጋዊ ሰውነት ዘለአለማዊ እና ፍጹም ይሆናል (አልማ ፲፩፥፵፭ት. እና ቃ. ፻፴፰፥፲፮–፲፯)።

ክፉ መንፈሶች