ናዝሬት ደግሞም ኢየሱስ ክርስቶስ ተመልከቱ በገሊላ ባህር በስተምዕራብ በኮረብታዎች መካከል የምትገኝ መንድር። ናዝሬት የክርስቶስ የመጀመሪያ መኖሪያ ቦታ ነበር (ማቴ. ፪፥፳፫)። ኢየሱስ በናዝሬት በምኩራብ ውስጥ አስተማረ፣ እናም በኢሳይያስ ፷፩፥፩–፪ ውስጥ ያለውን ትንቢት እንዳሟላ አወጀ (ማቴ. ፲፫፥፶፬–፶፰፤ ማር. ፮፥፩–፮፤ ሉቃ. ፬፥፲፮–፴)።