ጣኦት አምላኪ ጣኦት ማምለክ ወይም ከማንኛውም ነገር ጋር ከመጠን በላይ መያያዝ ወይም አምልኮ መኖር። ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ, ዘፀአ. ፳፥፫ (ሞዛያ ፲፪፥፴፭; ፲፫፥፲፪–፲፫). ሌሎችንም አማልክት ብትከተሉ፣ ፈጽሞ ትጠፋላችሁ, ዘዳግ. ፰፥፲፱. እልከኝነትም ጣዖትንና ተራፊምን እንደ ማምለክ ነው, ፩ ሳሙ. ፲፭፥፳፫. እኔን ትተሽ ለሌላ ተገልጠሻል, ኢሳ. ፶፯፥፰. ከብርና ከወርቅም የተሠሩትን አማልክት አመሰገንህ, ዳን. ፭፥፳፫. ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም, ማቴ. ፮፥፳፬. ጣኦትንም ማምለክ የሆነ መጎምጀት ነው, ቄላ. ፫፥፭. ልጆች ሆይ፥ ከጣዖታት ራሳችሁን ጠብቁ, ፩ ዮሐ. ፭፥፳፩. አዎን፣ ጣኦትን ለሚያመልኩ ወዮላቸው, ፪ ኔፊ ፱፥፴፯. የኔፊ ህዝብ ጣኦት አምላኪነት በእነርሱም ላይ ጦርነት እና ጥፋትን አምጥቶባቸው ነበር, አልማ ፶፥፳፩. እያንዳንዱ ሰው በአምላኩ መንገድ ይጓዛል, ት. እና ቃ. ፩፥፲፮. የጣኦት ማምለክ እንንዳይኖር በገዛ እጆቻቸው ይስሩ, ት. እና ቃ. ፶፪፥፴፱. የአብርሐም አባት ወደ ጣኦት አምልኮ ተወሰደ, አብር. ፩፥፳፯.