ማዳመጥ ደግሞም ታዛዥነት፣ ታዛዥ፣ መታዘዝ; ጆሮ ተመልከቱ የጌታን ድምፅ ወይም ትምህርትን ጌታ እንደ ሙሴ ያለ ነቢይ ያስነሣልሃል፤ እርሱንም ታደምጣለህ, ዘዳግ. ፲፰፥፲፭. ማዳመጥም የአውራ በግ ስብ ከማቅረብ ይበልጣል, ፩ ሳሙ. ፲፭፥፳–፳፫. የጌታ ባሪያዎችህን ነቢያትን አልሰማንም, ዳን. ፱፥፮. የነቢያትን ቃል የሚሰሙ ጻድቃኖች፣ እነርሱም የማይጠፉት ናቸው, ፪ ኔፊ ፳፮፥፰. የመልካሙን እረኛ ድምፅ የማትሰሙ ከሆነ፣ እናንተ የእርሱ በግ አይደላችሁም, አልማ ፭፥፴፰ (ሔለ. ፯፥፲፰). አቤቱ፣ እናንተ የቤተክርስቲያኔ ሰዎች ሆይ አድምጡ, ት. እና ቃ. ፩፥፩. የመንፈስን ድምፅ የሚያዳምጠውን ሰው ሁሉ ያብራራለታል እናም ወደ አብም ይመጣል, ት. እና ቃ. ፹፬፥፵፮–፵፯. የጌታ አምላካቸውን ድምፅ ለማድመጥ ይዘገዩ ነበር፤ ስለዚህ፣ ጌታ አምላካቸው ጸሎታቸውን ለማድመጥ ዘግይቷል, ት. እና ቃ. ፻፩፥፯–፱. ትእዛዛትን ያላዳመጡትም ተገስጸዋል, ት. እና ቃ. ፻፫፥፬ (ሙሴ ፬፥፬).