የጥናት እርዳታዎች
ይሳኮር


ይሳኮር

በብሉይ ኪዳን ውስጥ የያዕቆብና የልያ ወንድ ልጅ (ዘፍጥ. ፴፥፲፯–፲፰፴፭፥፳፫፵፮፥፲፫)። የእርሱ ትውልዶች ከእስራኤል አስራ ሁለት ጎሳዎች አንዱ ሆነ።

የይሳኮር ጎሳዎች

ለይሳኮር የተሰጠው የያዕቆብ በረከት በዘፍጥረት ፵፱፥፲፬–፲፭ ውስጥ ይገኛል። በከነዓን ከሰፈሩ በኋላ፣ ከእስድሬሎን ሜዳ በተጨማሪ እጅግ በጣም ሀብታም የፍልስጥኤምን ምድር ጎሳው ተቀበለ። በይሳኮር ድንበር ውስጥ በአይሁዳ ታሪክ ውስጥ አስፈላጊ የሆኑ ብዙ ቦታዎች ነበሩ፣ ለምሳሌ፣ ቀርሜሎስ፣ መጊዶ፣ ዶታይን፣ ጊልቦዓ፣ ኢይዝራኤል፣ ታቦር፣ እና ናዝሬት (ኢያ. ፲፱፥፲፯–፳፫)