መቃብር ደግሞም ትንሳኤ ተመልከቱ የምድራዊ ሰውነት መቀበሪያ ቦታ። በኃጢያት ክፍያ ምክንያት፣ እያንዳንዱ ሰው ከመቃብር በትንሳኤ ይነሳል። ክርስቶስ ከሞት ከተነሳ በኋላ፣ መቃብሮች ተከፈቱ እና ብዙ ሰውነቶች ተነሱ, ማቴ. ፳፯፥፶፪–፶፫ (፫ ኔፊ ፳፫፥፱–፲፫). ሲኦል ሆይ፥ ድል መንሣትህ የት አለ, ፩ ቆሮ. ፲፭፥፶፭. መቃብርም የያዘቻቸውን አካላት ማስረከብ አለባት, ፪ ኔፊ ፱፥፲፩–፲፫. በመቃብራቸው የሚያነቀላፉትም ይመጣሉ, ት. እና ቃ. ፹፰፥፺፯–፺፰. የማጥመቂያም ገንዳ የመቃብር ምሳሌ ነው, ት. እና ቃ. ፻፳፰፥፲፪–፲፫.