ክህነት ደግሞም ሀይል; መሾም፣ ሹመት; ስልጣን; አሮናዊ ክህነት; የመልከ ጼዴቅ ክህነት; የክህነት መሀላ እና ቃል ኪዳን; የክህነት ቁልፎች ተመልከቱ ለሰው ደህንነት በሁሉም ነገሮች ሰዎች ለመስራት እንዲችሉ እግዚአብሔር ለሰው የሚሰጠው ስልጣን እና ሀይል (ት. እና ቃ. ፶፥፳፮–፳፯)። የክህነት ባለስልጣን የሆኑ የቤተክርስቲያኗ ወንድ አባላት በቡድኖች ተደራጅተዋል እናም በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ስነስርዓቶችንና ማስተዳደሪያ ስራዎችን ለማከናወን ስልጣን አላቸው። መቀባታቸውም ለዘላለም ክህነት ይሆንላቸዋል, ዘፀአ. ፵፥፲፭ (ዘኁል. ፳፭፥፲፫). ሾምኋችሁ, ዮሐ. ፲፭፥፲፮. ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ, ፩ ጴጥ. ፪፥፭. እናንተ የጠራችሁን ትውልድ የንጉሥ ካህናት ናችሁ, ፩ ጴጥ. ፪፥፱ (ዘፀአ. ፲፱፥፮). በእምነታቸው እና በታላቅ ስራቸው ምክንያት ሰዎች እንደ ሊቀ ካህናት ተጠርተዋል, አልማ ፲፫፥፩–፲፪. እንድታጠምቅ ስልጣንን እሰጥሃለሁ, ፫ ኔፊ ፲፩፥፳፩. መንፈስ ቅዱስንም ለመስጠት ስልጣን ይኖራችኋል, ሞሮኒ ፪፥፪. በኤሊያስ እጅ ክህነትን እገልጽላችኋለሁ, ት. እና ቃ. ፪፥፩ (ጆ.ስ.—ታ. ፩፥፴፰). ጌታ ክህነትን በአሮን እና በዘሮቹ ላይ አረጋገጠ, ት. እና ቃ. ፹፬፥፲፰. ይህም ታላቅ ክህነት ወንጌሉን ያስተዳድራል, ት. እና ቃ. ፹፬፥፲፱. ሙሴን፣ እናም ደግሞም ቅዱስ ክህነትን፣ ከመካከላቸው አወጣ, ት. እና ቃ. ፹፬፥፳፭. የክህነት መሀላ እና ቃል ኪዳን ተገልጿል, ት. እና ቃ. ፹፬፥፴፫–፵፪. በአባቶቻችሁ ዘር ክህነት ቀጥለዋል, ት. እና ቃ. ፹፮፥፰. በቤተክርስቲያኗ ውስጥ፣ ሁለት የክህነት ባለስልጣኖች አሉ, ት. እና ቃ. ፻፯፥፩. የመጀመሪያው ክህነት፣ እንደ እግዚአብሔር ልጅ ስርዓት ቅዱስ ክህነት ነው, ት. እና ቃ. ፻፯፥፪–፬. የክህነት መብቶች እና የሰማይ ሀይሎች የማይነጣጠሉ ናቸው, ት. እና ቃ. ፻፳፩፥፴፮. በማሳመን እና ግብዝነት በሌለው ፍቅር ካልሆነ በስተቀር፣ ምንም ሀይል ወይም ተጽዕኖ በክህነት ስልጣን ዘዴ ሊደገፍ አይቻልም ወይም አይገባም, ት. እና ቃ. ፻፳፩፥፵፩. እያንዳንዱ ታማኝ፣ ብቁ ወንድ የቤተክርስቲያኗ አባል ክህነትን ይቀበላል, አ.አ. ፪. ወንድ በእግዚአብሔር መጠራት አለበት, እ.አ. ፩፥፭.