የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ደግሞም የቤተክርስቲያን ስም; የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን; የእውነተኛ ቤተክርስቲያን ምልክቶች; የወንጌል ዳግም መመለስ ተመልከቱ የኋለኛው ቀናት የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን ከሌላው ዘመን ቤተክርስቲያናት ለመለየት የተሰጠ ስም፣ (ት. እና ቃ. ፻፲፭፥፫–፬)። ጌታ እውቀቶችን በኋለኛው ቀን ቅዱሳን ላይ ያፈስሣል, ት. እና ቃ. ፻፳፩፥፴፫. ጆሴፍ ስሚዝ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ነቢይና ባለራዕይ ነው, ት. እና ቃ. ፻፳፯፥፲፪. የጌታ ታላቅ ቀን ለኋለኛው ቀን ቅዱሳን ደርሷል, ት. እና ቃ. ፻፳፰፥፳፩፣ ፳፬. ጆሴፍ ስሚዝ የኋለኛው ቀን ቅዱሳንን ለመሰብሰብ ረዳ, ት. እና ቃ. ፻፴፭፥፫. የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ወደ ደቡብ ዩናይትድ ስቴትስ ክፍለ አገሮች ለመኋዝ በቡድን ተደራጁ, ት. እና ቃ. ፻፴፮፥፪. የጋብቻ ህግጋት ለኋለኛው ቀን ቅዱሳን ተገለጹ, አ.አ. ፩. ለኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ብቁ ለሆኑ ወንድ አባላት በሙሉ ክህነት ተሰጠ, አ.አ. ፪. ለኋለኛው ቀን ቅዱሳን የተሰጠ የመጀመሪያው ራዕይ ታሪክ, ጆ.ስ.—ታ. ፩፥፩.