ጸብ ደግሞም አመጽ ተመልከቱ ጠብ፣ ሁከታ፣ መከራከር፣ መጨቃጨቅ፣ እና ክርክር። ጸብ፣ በልዩም በጌታ ቤተክርስቲያን አባላትና በቤተሰብ አባላት መካከል፣ ጌታን የሚያስደስት አይደለም። በእኔና በአንተ መካከል ጠብ አይኑር, ዘፍጥ. ፲፫፥፰. በትዕቢት ጠብ ብቻ ይሆናል, ምሳ. ፲፫፥፲. ማንም በባልንጀራው ላይ የሚነቅፈው ነገር ካለው፣ ክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ እናንተም ይቅር በሉ, ቄላ. ፫፥፲፫. ሞኝነት ካለው ምርመራና ከጠብ ራቅ, ቲቶ ፫፥፱. ጌታ ሰዎችን እርስ በራስ እንዳይጣሉ አዘዘ, ፪ ኔፊ ፳፮፥፴፪. ልጆቻችሁ እርስ በርሳቸውም እንዲጣሉ አትፍቀዱ, ሞዛያ ፬፥፲፬. አልማ በቤተክርስቲያን አባላት መካከል ጸብ እንዳይኖር አዘዘ, ሞዛያ ፲፰፥፳፩. ሰይጣን አሉባልታን፣ እናም ፀብን ያሰራጫል, ሔለ. ፲፮፥፳፪. ዲያብሎስ የፀብ አባት ነው እናም የሰዎችን ልብ እርስ በርስ እንዲጣሉ ያደርጋል, ፫ ኔፊ ፲፩፥፳፱ (ሞዛያ ፳፫፥፲፭). ብዙ ጸብ እንዳይኖር ወንጌሌን መስርቱ, ት. እና ቃ. ፲፥፷፪–፷፬. እርስ በራስም መጣላትን አቁሙ, ት. እና ቃ. ፻፴፮፥፳፫.