ስልጣን ደግሞም ሀይል; መሾም፣ ሹመት; ክህነት; የክህነት ቁልፎች; ጥሪ፣ በእግዚአብሔር መጠራት፣ የተጠራበት ተመልከቱ የእግዚአብሔር ስራን ለማከናወን በምድር ላይ ለእግዚአብሔር አብ ወይም ለኢየሱስ ክርስቶስ እና በስማቸው ለመስራት ለተጠሩት ወይም ለተሾሙት ሰዎች የተሰጠ ፈቃድ። ልኬሀለሁ, ዘፀአ. ፫፥፲፪–፲፭. ያዘዝሁህን ነገር ሁሉ አንተ ትነግረዋለህ, ዘፀአ. ፯፥፪. አሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርቱን ሥልጣን ሰጣቸው, ማቴ. ፲፥፩. እኔ መረጥኋችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፣ እና ሾምኋችሁ, ዮሐ. ፲፭፥፲፮. ኔፊና ሌሒ በታላቅ ኃይልና ስልጣን ሰበኩ, ሔለ. ፭፥፲፰. የሔለመን ወንድ ልጅ ኔፊ የእግዚአብሔር ሰው፣ ታላቅ ኃይልና ስልጣን ከእግዚአብሔር የተሰጠው ነበር, ሔለ. ፲፩፥፲፰ (፫ ኔፊ ፯፥፲፯). ኢየሱስ ለአስራ ሁለቱ ኔፋውያን ሀይልና ስልጣን ሰጣቸው, ፫ ኔፊ ፲፪፥፩–፪. ጆሴፍ ስሚዝ በእግዚአብሔር ተጠርቶና ተሹሞ ነበር, ት. እና ቃ. ፳፥፪. ካልተሾመ፣ እና ስልጣን እንዳለው በቤተክርስቲያኗ የሚታወቅ ካልሆነ በስተቀር፣ ለማንም ወንጌሌን እንዲሰብክ ወይም ቤተክርስቲያኔን እንዲገንባ አይሰጠውም, ት. እና ቃ. ፵፪፥፲፩. ሽማግሌዎች በስልጣን እየሰሩ ወንጌሉን ይስበኩ, ት. እና ቃ. ፷፰፥፰. የመልከ ጼዴቅ ክህነት በመንፈሳዊ ነገሮች ለማስተዳደር ስልጣን አለው, ት. እና ቃ. ፻፯፥፰፣ ፲፰–፲፱. በመለኮታዊ ስልጣን የተደረገው ህግ ይሆናል, ት. እና ቃ. ፻፳፰፥፱. የሚሰብክ ወይም ለእግዚአብሔር የሚያገለግል ስልጣን ባላቸው በእግዚአብሔር መጠራት አለበት, እ.አ. ፩፥፭.