የጥናት እርዳታዎች
የታላቅ ዋጋ ዕንቁ


የታላቅ ዋጋ ዕንቁ

በምድር ላይ ያለው የእግዚአብሔር መንግስት “ታላቅ ዋጋ ካለው ዕንቁ” ጋር ተመሳስሏል (ማቴ. ፲፫፥፵፭–፵፮)።

የታላቅ ዋጋ ዕንቁ ይፋ ከሆኑት ከኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አራት ቅዱሣት መጻህፍት መካከል ለአንዱ የተሰጠ ስም ነው። የታላቅ ዋጋ ዕንቁ በመጀመሪያ የታተመው በ፲፰፻፶፩ (እ.አ.አ.) ነበር እናም አሁን በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ውስጥ የሚገኙት አንዳንድ ነገሮችን ያለው ነበር። ከ፲፱፻፪ (እ.አ.አ.) ጀምሮ የታተሙት እትሞች (፩) ከጆሴፍ ስሚዝ የኦሪት ዘፍጥረት ትርጉም የተወሰዱ መፅሐፈ ሙሴ የሚባሉትን ክፍሎች፣ እና ጆሴፍ ስሚዝ—ማቴዎስ ተብሎ የሚጠራ የማቴዎስ ፳፬ን፤ (፪) በ፲፰፻፴፭ (እ.አ.አ.) ጆሴፍ ስሚዝ ከግብጻዊ ፓፓይረስ የተተረጎመ መፅሐፈ አብርሐም ተብሎ የሚታወቅ መፅሐፍን፤ (፫) በ፲፰፻፴፰ (እ.አ.አ.) የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ ተብለው የሚታወቁ ከጆሴፍ ስሚዝ የቤተክርስቲያኗ ታሪክ የተወሰዱ ታሪኮችን፤ እና (፬) አስራ ሶስት የእምነት እና የትምህርት መረጃዎች የሆንይትን የእምነት አንቀጾችን የያዘ ነው።