አዳኝ ደግሞም ኢየሱስ ክርስቶስ ተመልከቱ የሚያድን ኢየሱስ ክርስቶስ፣ በኃጢያት ክፍያ በኩል፣ ለሰው ዘር ቤዛነት እና ደህንነትን አቀረበ። “አዳኝ” የኢየሱስ ክርስቶስ ስም እና ርዕስ ነው። እግዚአብሔር ብርሃኔና መድኃኒቴ ነው, መዝ. ፳፯፥፩ (ዘፀአ. ፲፭፥፩–፪; ፪ ሳሙ. ፳፪፥፪–፫). እኔ፥ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥ ከእኔ ሌላም የሚያድን የለም, ኢሳ. ፵፫፥፲፩ (ት. እና ቃ. ፸፮፥፩). እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ, ማቴ. ፩፥፳፩. ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋል, ሉቃ. ፪፥፲፩. እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና, ዮሐ. ፫፥፲፮–፲፯. ከክርስቶስ በስተቀር ሰው የሚዳንበት ምንም ሌላ ስም የለም, የሐዋ. ፬፥፲–፲፪ (፪ ኔፊ ፳፭፥፳; ሞዛያ ፫፥፲፯; ፭፥፰; ት. እና ቃ. ፲፰፥፳፫; ሙሴ ፮፥፶፪). ከሰማይ መድኃኒትን፣ ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን እንጠባበቃለን, ፊልጵ. ፫፥፳. አባትም ልጁን የዓለም መድኃኒት ሊሆን ላከው, ፩ ዮሐ. ፬፥፲፬. ጌታ እግዚአብሔር መሲሁን፣ የዓለምን መድኃኒት ያስነሳል, ፩ ኔፊ ፲፥፬. የእግዚአብሔርም በግ የአለም አዳኝ እንደሆነ, ፩ ኔፊ ፲፫፥፵. የአዳኛችን እውቀት በሁሉም ሀገር፣ ነገድ፣ ቋንቋ እና ህዝብ መካከል ይሰራጫል, ሞዛያ ፫፥፳. ደህንነት እንዲመጣ ክርስቶስ መሞት ይገባዋል, ሔለ. ፲፬፥፲፭–፲፮. በአዳኛችን በኩል የሚገኘው ጽድቅነትና ቅድስና ትክክል እና እውነተኛ ናቸው, ት. እና ቃ. ፳፥፴–፴፩. እኔ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ የአለም አዳኝ ነኝ, ት. እና ቃ. ፵፫፥፴፬. አንድያ ልጄም አዳኝ ነው, ሙሴ ፩፥፮. በወልድ ያመኑትና ለኃጥያታቸው ንስሀ የገቡት ሁሉ ይድናሉ, ሙሴ ፭፥፲፭.