ፍቅር ደግሞም ልግስና; ርህራሄ; ጠላትነት ተመልከቱ ጥልቅ ታማኝነት እና የፍቅር ስሜት። ለእግዚአብሔር የሚኖር ፍቅር ታማኝነትን፣ ጥልቅ ፍቅርን፣ አምልኮትን፣ ለጋስነትን፣ ምህረትን፣ ይቅርታ መስጠትን፣ ርህራሄን፤ ጸጋን፣ አገልግሎትን፣ ምስጋናን፣ ደግነትን የሚጨምር ነው። እግዚአብሔር ለልጆቹ ያለው ፍቅር ታላቅ ምሳሌ የሚገኘው መጨረሻ በሌለው በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ ነው። ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ, ዘሌዋ. ፲፱፥፲፰ (ማቴ. ፭፥፵፫–፵፬; ፳፪፥፴፯–፵; ሮሜ ፲፫፥፱; ገላ. ፭፥፲፬; ያዕ. ፪፥፰; ሞዛያ ፳፫፥፲፭; ት. እና ቃ. ፶፱፥፮). አንተም አምላክህን እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ ውደድ, ዘዳግ. ፮፥፭ (ሞሮኒ ፲፥፴፪; ት. እና ቃ. ፶፱፥፭). አምላካችሁን እግዚአብሔርን ትወድዱት እንደ ሆነ ያውቅ ዘንድ ሊፈትናችሁ ነው, ዘዳግ. ፲፫፥፫. እግዚአብሔር የወደደውን ይገሥጻልና, ምሳ. ፫፥፲፪. ወዳጅ በዘመኑ ሁሉ ይወድዳል, ምሳ. ፲፯፥፲፯. እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና, ዮሐ. ፫፥፲፮ (ት. እና ቃ. ፻፴፰፥፫). እንደ ወደድኋችሁ እናንተ ደግሞ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ, ዮሐ. ፲፫፥፴፬ (ዮሐ. ፲፭፥፲፪፣ ፲፯; ሙሴ ፯፥፴፫). ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ, ዮሐ. ፲፬፥፲፭ (ት. እና ቃ. ፵፪፥፳፱). ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም, ዮሐ. ፲፭፥፲፫. ጴጥሮስ ከእነዚህ ይልቅ ትወደኛለህን? በጎቼን አሰማራ, ዮሐ. ፳፩፥፲፭–፲፯. በክርስቶስ ኢየሱስ ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን ምንም አይችልም, ሮሜ ፰፥፴፭–፴፱. ዓይን ያላየችው ጆሮም ያልሰማውን እግዚአብሔር ለሚወዱት ያዘጋጀው, ፩ ቆሮ. ፪፥፱. በፍቅር እርስ በርሳችሁ እንደ ባሪያዎች ሁኑ, ገላ. ፭፥፲፫. ባሎች ሆይ፥ ሚስቶቻችሁን ውደዱ, ኤፌ. ፭፥፳፭ (ቄላ. ፫፥፲፱). ዓለምን አትውደዱ, ፩ ዮሐ. ፪፥፲፭. እግዚአብሔር ፍቅር ነው, ፩ ዮሐ. ፬፥፰. እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና እኛ እንወደዋለን, ፩ ዮሐ. ፬፥፲፱. ክርስቶስ በቸርነቱ ምክንያት ይሰቃያል, ፩ ኔፊ ፲፱፥፱. የእግዚአብሔርና የሰዎች ሁሉ ፍቅር እየኖራችሁ መቀጠል አለባችሁ, ፪ ኔፊ ፴፩፥፳. ልጆቻችሁን እርስ በርሳቸው እንዲዋደዱ እንዲሁም አንደኛው ሌላኛውን እንዲያገለግል ታስተምሯቸዋላችሁ, ሞዛያ ፬፥፲፭. የአዳኛችሁን የፍቅር ዜማ ለመዘመር ከተሰማችሁ፣ አሁንም ሊሰማችሁ ይችላልን, አልማ ፭፥፳፮. ታጋሽ፣ ፍቅር የሞላባችሁ በመሆን በመንፈስ ቅዱስ የምትመሩ እንድትሆኑ እመኛለሁ, አልማ ፲፫፥፳፰. በፍቅር ትሞላ ዘንድ ስሜትህን በሙሉ ተቆጣጠር, አልማ ፴፰፥፲፪. በህዝቡ ልብ ውስጥ ባለው የእግዚአብሔር ፍቅር የተነሳ በምድሪቱ ፀብ አልነበረም, ፬ ኔፊ ፩፥፲፭. እግዚአብሔርን ለመውደድ የሚጋብዝ ሁሉ በእግዚአብሔር የተነሳሳ ነው, ሞሮኒ ፯፥፲፫–፲፮. ልግስና ንፁህ የክርስቶስ ፍቅር ነው, ሞሮኒ ፯፥፵፯. ፍፁም የሆነ ፍቅር ፍርሃትን ሁሉ አውጥቶ ይጥላል, ሞሮኒ ፰፥፲፮ (፩ ዮሐ. ፬፥፲፰). ፍቅር ሰዎችን ለእግዚአብሔር ስራ ብቁ ያደርጋሉ, ት. እና ቃ. ፬፥፭ (ት. እና ቃ. ፲፪፥፰). ቅድስና እግዚአብሔርን አፍቅረው ለሚያገለግሉት ሁሉ ይመጣል, ት. እና ቃ. ፳፥፴፩. ከወደዳችሁኝ ታገለግሉኛላችሁ እናም ሁሉንም ትዛዛቶቼን ትጠብቃላችሁ, ት. እና ቃ. ፵፪፥፳፱ (ዮሐ. ፲፬፥፲፭). ለተቆጣኸውም ተጨማሪ ፍቅር አሳይ, ት. እና ቃ. ፻፳፩፥፵፫. ሰዎች ስይጣንን ከእግዚአብሔር በላይ ወደዱ, ሙሴ ፭፥፲፫፣ ፲፰፣ ፳፰.