የጥናት እርዳታዎች
ወደ ተሰሎንቄ መልእክት


ወደ ተሰሎንቄ መልእክት

በአዲስ ኪዳን ውስጥ ያሉ ሁለት መጻህፍት። እነዚህ ጳውሎስ በ፶ ም.ዓ. አካባቢ አውሮፓን በጎበኘበት ጊዜ በቆሮንቶስ ውስጥ እያለ በመጀመሪያ ለተሰሎንቄ የጻፋቸው ደብዳቤዎች ነበሩ። በተሰሎንቄ የነበረው ስራ በ የሐዋርያት ስራ ፲፯ ውስጥ ተዘርዝረዋል። ጳውሎስ ወደ ተሰሎንቄ ለመመለስ ፈለገ ነገር ግን ይህን ለማድረግ አልቻለም ነበር (፩ ተሰ. ፪፥፲፰)። ስለዚህ የተቀየሩትን እንዲያስደስት እና እንዴት እንደሆኑ መልእክት እንዲያመጣለት ጢሞቴዎስን ላከ። ጳውሎስ የመጀመሪያውን መልእክት የጻፈው በጢሞቴዎስ መመለስ ምስጋና ስለተሰማው ነበር።

መጀመሪያይቱ ተሰሎንቄ

ምዕራፍ ፩–፪ የጳውሎስን ሰላምታ እና ለቅዱሳን ያለውን ጸሎት የያዙ ነበሩ፤ ምዕራፍ ፫–፭ ስለመንፈሳዊ እድገት፣ ፍቅር፣ ንጹህነት፣ ትጋት፣ እና ስለኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምፅዓት መመሪያዎች የሚሰጡ ነበሩ።

ሁለተኛይቱ ተሰሎንቄ

ምዕራፍ ፩ ለቅዱሳን የነበረውን ጸሎት የያዘ ነበር። ምዕራፍ ፪ ስለሚመጣው ክህደት ተናግሯል። ምዕራፍ ፫ ለመንጌሉ ምክንያት ድል ማግኘት የነበረውን የጳውሎስ ጸሎትን የያዘ ነበር።