እግዚአብሔርን የሚጠላ ደግሞም ኃጢያተኛ፣ አመፃ; ኃጢያት; እድፍ፣ እድፍነት; ክፉ፣ ክፋት ተመልከቱ በእግዚአብሔር ፍላጎት ወይም ትእዛዛት መሰረት ያልሆነ አንድ ሰው ወይም አንድ ነገር፤ ክፉ እና ያልተቀደሰ። የክፉዎች መንገድ ግን ትጠፋለች, መዝ. ፩፥፮. ጻድቅም በጭንቅ የሚድን ከሆነ ዓመፀኛውና ኃጢአተኛው ወዴት ይታይ, ፩ ጴጥ. ፬፥፲፰. ኃጢአተኝነትን በሙሉ ለእራሳችሁ ካዱ, ሞሮኒ ፲፥፴፪. በኀጥያተኞቹ ላይ በቀል በቶሎ መጥቷል, ት. እና ቃ. ፺፯፥፳፪. እግዚአብሔርን በሚጠሉት መካከል ድምጹ አለተነሳም, ት. እና ቃ. ፻፴፰፥፳.