ጌቴሴማኒ ደግሞም የኃጢያት ዋጋን መክፈል፣ የኃጢያት ክፍያ; ደብረ ዘይት ተራራ ተመልከቱ በአዲስ ኪዳን ውስጥ በደብረ ዘይት ተራራ አጠገብ የሚገኝ የአትክልት ስፍራ። በአራሜያዊ ቋንቋ፣ ጌቴሴማኒ “የወይራ መጭመቂያ” ማለት ነው። ኢየሱስ ይሁዳ በካደው ምሽት ወደ አትክልት ስፍራው ሄደ። በእዚያም ጸለየ እናም በጌቴሴማኒ ውስጥ ለሰው ዘር ኃጢያቶች ተሰቃየ (ማቴ. ፳፮፥፴፮፣ ፴፱፤ ማር. ፲፬፥፴፪፤ ዮሐ. ፲፰፥፩፤ አልማ ፳፩፥፱፤ ት. እና ቃ. ፲፱፥፲፭–፲፱)።