የጥናት እርዳታዎች
ገሊላ


ገሊላ

በጥንት እና በዚህም ዘመን፣ በዮርዳኖስ ወንዝና በገሊላ ባህር በስተምዕራብ የሚገኝ የእስራኤል ሰሜናዊ አውራጃ። ገሊላ ዘጠና ሰባት ኪሎ ሜትር ረጅምና አርባ ስምንት ኪሎ ሜትር ስፋት ያለው ነው። በጥንት ጊዜ፣ ከሁሉም በላይ ጥሩ የሆኑ ምድርንና ከእስራኤል ከተማዎች በላይ በጣም ስራ የበዙባቸው ከተማዎችን የያዘ ነው። ወደ ደማስቆ፣ ወደ ግብፅ፣ እና ወደ ምስራቅ እስራኤል የሚመሩ አውራ መንገዶች በገሊላ በኩል ያልፋሉ። ጥሩም የአየር ጠባዩ እና የለማ አፈሩ ብዙ ወይራ፣ ስንዴ፣ ገብስና፣ ወይኖች ያሳድጋሉ። በገሊላ ባህር የሚገኙት የአሳ ማርቢያዎች ብዙ ወደ ውጪ ሀገር የሚሸጡትን ያስገኛሉ እናም የታላቅ ሀብት ምንጭ ነበሩ። ጌታ ብዙ ጊዜውን በገሊላ ውስጥ አሳለፈ።

የገሊላ ባህር

የገሊላ ባህር በሰሜን እስራኤል የሚገኝ ነው። ይህም በብሉይ ኪዳን ውስጥ ኪኔሬት ባሕር እና በአዲስ ኪዳን ውስጥ የጌንሴሬጥ ሀይቅ ወይም ጥብርያዶስ ተብሎ ይጠራል። ኢየሱስ ብዙ ስብከቱን በእዚያ አደረገ (ማቴ. ፲፫፥፪)። ባህሩ ሸክኒት አይነት ቅርጽ የነበረው፣ ፳ ኪሎ ሜትር ረጅም እና ሰፊ በሆነበት ቦታ ላይ ፲፪ ኪሎ ሜትር የሰፋ ነበር። ከባህር አማካይ ጥልቀት ከ፪፻፯ ሜትር በታች ይገኛል፣ ይህም በአካባቢው የሚገኘውን አየር በጣም የሞቀ ያደርገዋል። ቀዝቃዛ አየሩ ከኩረብታው ወደታች ወርዶ ከውሀው በላይ ከሚገኘው ሙቅ ውሀ ጋር በመገናኘት የድንገት ሀይለኛ ዝናብ ይጀምራል (ሉቃ. ፰፥፳፪–፳፬)።