በኩር
በጥንት ፓትሪያርኮች ዘመን፣ በመጀመሪያ የተወለደ ልጅ በኩርን ይቀበላል (ዘፍጥ. ፵፫፥፴፫) እና በዚህ አባትየው በሚሞትበት ጊዜ የቤተሰብ አመራርን ይወርሳል። በኩር ይህን ሀላፊነት ለመቀበል ብቁ መሆን አለበት (፩ ዜና ፭፥፩–፪) እናም በኩሩን ጻድቅ ባለመሆን ለማጣት ይችላል። የመውረስ መብት የበኩር ልጅ ነው። በአጠቃላይ፣ በኩርነት በቤተሰብ ወይም ባህል ውስጥ ለተወለደው የሚተላለፈውን ማንኛውንም ወይም ሁሉንም መብቶች ወይም ውርስ ያጠቃልላል።
በሙሴ ህግጋት ስር፣ በመጀመሪያ የተወለደው ልጅ የእግዚአብሔር እንደሆነ ይታሰብበታል። በኩር ከአባቱ ንብረቶች ሁለት እጥፍ ይቀበላሉ (ዘዳግ. ፳፩፥፲፯)። አባቱ ከሞተ በኋላ፣ ለእናቱና ለእህቶቹ መንከባከብ ሀላፊነት ይኖረዋል።
በመጀምሪያ የተወለደ ወንድ እንስሣት የእግዚአብሔር ነው። ንጹህ እንስሳት ለመስዋዕት ይጠቀሙባቸዋል፣ ንጹህ ያልሆኑ እንስሳት ግን ይድናሉ፣ ወይም ይሸጣሉ ወይም ይገደላሉ (ዘፀአ. ፲፫፥፪፣ ፲፩–፲፫፤ ፴፬፥፲፱–፳፤ ዘሌዋ. ፳፯፥፲፩–፲፫፣ ፳፮–፳፯)።
በኩር ኢየሱስ ክርስቶስን እና የምድር አገልግሉቱን ያመሳስላሉ፣ ይህም ታላቁ መሲህ እንደሚመጣ ህዝቦችን እንዲያስታውሱ ያደርጋል (ሙሴ ፭፥፬–፰፤ ፮፥፷፫)።
ኢየሱስ ከሰማይ አባታችን መንፈስ ልጆች በመጀመሪያ የተወለደ፣ የአብ በስጋ አንድያ ልጅ፣ እና ከሞት በትንሳኤ በመነሳት የመጀመሪያው ነው (ቄላ. ፩፥፲፫–፲፰)። ታማኝ ቅዱሳን የበኩር ቤተክርስቲያን ለዘለአለም አባል ይሆናሉ (ት. እና ቃ. ፺፫፥፳፩–፳፪)።