ህያው ማድረግ ደግሞም ትንሳኤ ተመልከቱ ህያው ማድረግ፣ ከሞት ማስነሳት፣ ወይም በእግዚአብሔር ፊት ለመገኘት እንዲችል ሰውን መቀየር። እግዚአብሔር ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን, ኤፌ. ፪፥፬–፭ (ቄላ. ፪፥፮፣ ፲፪–፲፫). ክርስቶስ በሥጋ ሞተ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ, ፩ ጴጥ. ፫፥፲፰ (ት. እና ቃ. ፻፴፰፥፯). በእግዚአብሔር መንፈስ የተነሳሱ ካልሆኑ በስተቀር፣ በስጋ እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም, ት. እና ቃ. ፷፯፥፲፩. የነፍስ ቤዛነትም ሁሉንም ነገሮች ህይወት በሚሰጠው ነው, ት. እና ቃ. ፹፰፥፲፮–፲፯. ህያው የሆኑት፣ ከክርስቶስ ጋር ይነጠቃሉ, ት. እና ቃ. ፹፰፥፺፮. አዳም በውስጥ ሰውነትም ህይወት ተሰጠው, ሙሴ ፮፥፷፭.