የጥናት እርዳታዎች
ዮሴፍ፣ የማርያም ባለቤት


ዮሴፍ፣ የማርያም ባለቤት

የኢየሱስ እናት ማርያም ባለቤት። ዮሴፍ የዳዊት ዘር (ማቴ. ፩፥፩–፲፮ሉቃ. ፫፥፳፫–፴፰) እናም በናዝሬት ይኖር ነበር። ከማርያም ጋር የተዳረ ነበር። ከጋብቻቸው በፊት፣ ማርያም የአዳኝ እናት እንድትሆን እንደተመረጠች ባስታወቃት በመልአኩ ገብርኤል ማርያም ተጎበኘች (ሉቃ. ፩፥፳፮–፴፭)። ዮሴፍ ስለዚህ መለኮታዊ ውልደት ራዕይን ተቀበለ (ማቴ. ፩፥፳–፳፭)።

ማርያም የኢየሱስ ብቸኛ ወላጅ ነበረች ምክንያቱም እግዚአብሔር የኢየሱስ አባት ነውና። ነገር ግን አይሁዶች ዮሴፍን እንደ ኢየሱስ አባት ያስቡት ነበር፣ ኢየሱስንም እንደዚህ ነበር የሚያስቡት (ሉቃ. ፪፥፵፰፣ ፶፩)። በሰማያዊ ህልሞች ማስጠንቀቂያ በመቀበል፣ ዮሴፍ የህጻን ኢየሱስን ህይወት ወደ ግብፅ በመሸሽ አዳነ (ማቴ. ፪፥፲፫–፲፬)። ሄሮድስ ከሞተ በኋላ፣ መልአክ ዮሴፍ ኢየሱስን ወደ እስራኤል እንዲወስድ መመሪያ ሰጠው (ማቴ. ፪፥፲፱–፳፫)።