መምረጥ፣ መረጠ፣ የተመረጠ (ግስ) ደግሞም ነጻ ምርጫ; ነጻ፣ ነጻነት; ጥሪ፣ በእግዚአብሔር መጠራት፣ የተጠራበት ተመልከቱ ጌታ ግለሰብን ወይም ቡድንን በሚመርጥበት ወይም በሚወስንበት ጊዜ፣ ደግሞም በአብዛኛው ጊዜ እነርሱን እንዲያገለግሉ ይጠራል። የምታገለግለውን ዛሬ ምረጡ, ኢያ. ፳፬፥፲፭ (አልማ ፴፥፰; ሙሴ ፮፥፴፫). በመከራም እቶን መርጬሀለሁ, ኢሳ. ፵፰፥፲ (፩ ኔፊ ፳፥፲). የተጠሩ ብዙዎች፥ የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸው, ማቴ. ፳፪፥፲፬ (ማቴ. ፳፥፲፮; ት. እና ቃ. ፺፭፥፭; ፻፳፩፥፴፬፣ ፵). እኔ መረጥኋችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም, ዮሐ. ፲፭፥፲፮. እግዚአብሔር ጥበበኞችን እንዲያሳፍር የዓለምን ሞኝ ነገር መረጠ, ፩ ቆሮ. ፩፥፳፯. ዓለም ሳይፈጠር በፊት መርጦናል, ኤፌ. ፩፥፬. ነፃነትን ወይም ዘለዓለማዊ ህይወትን ለመምረጥ፣ ወይም ምርኮንና ሞትን ለመምረጥ ነፃ ነን, ፪ ኔፊ ፪፥፳፯. የተከበሩትና ታላቆቹ በመጀመሪያ ተመርጠው ነበር, ት. እና ቃ. ፻፴፰፥፶፭–፶፮. እስራኤል በእግዚአብሔር ተመርጣ ነበር, ሙሴ ፩፥፳፮. አብርሐም ከመወለዱ በፊት ተመርጦ ነበር, አብር. ፫፥፳፫.