ሀብቶች ደግሞም ኩራት; ገንዘብ ተመልከቱ መትረፍረፍ ወይም ሀብት። ጌታ ቅዱሳንን በእነዚያ ጥሩ ለማድረግ ካልሆነ በቀር አለማዊ ሀብቶችን እንዳይፈልጉ መክሯል። ቅዱሳን የአለም ሀብትን ከመፈለጋቸው በፊት፣ የዘለአለም ሀብቶች የያዘውን የእግዚአብሔር መንግስት መፈልግ ይገባቸዋል፣ (ያዕቆ. ፪፥፲፰–፲፱)። ባለጠግነት ቢበዛ ልባችሁ አይኵራ, መዝ. ፷፪፥፲. በቍጣ ቀን ሀብት አትረባም, ምሳ. ፲፩፥፬. በባለጠግነቱ የሚተማመን ሰው ይወድቃል, ምሳ. ፲፩፥፳፰. መልካም ስም ከብዙ ባለጠግነት ይሻላል, ምሳ. ፳፪፥፩. ገንዘብ ላላቸው ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት እንዴት ጭንቅ ይሆናል, ማር. ፲፥፳፫ (ሉቃ. ፲፰፥፳፬–፳፭). ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ሥር ነው, ፩ ጢሞ. ፮፥፲. ሀብታም በመሆናቸው ድሆችን ለሚጠሉት ወዮላቸው, ፪ ኔፊ ፱፥፴. ጻድቃን ልባቸውን በሀብቶች ላይ አላስቀመጡም ነገር ግን ከሁሉም ጋር ተካፈሉ, አልማ ፩፥፴. ህዝቦች በሀብቶቻቸው ምክንያት መኩራት ጀመሩ, አልማ ፬፥፮–፰. ህዝቡ እንደ ሀብቱ መሰረት በደረጃ መከፋፈል ጀመሩ, ፫ ኔፊ ፮፥፲፪. ጥበብን እንጂ ሃብትን አትሹ, ት. እና ቃ. ፮፥፯ (አልማ ፴፱፥፲፬; ት. እና ቃ. ፲፩፥፯). የምድር ሃብት ሁሉ ለመስጠት እግዚአብሔር ነው፤ ነገር ግን ኩራትን ተጠንቀቁ, ት. እና ቃ. ፴፰፥፴፱. የዘለአለም ሀብቶች በሰማይ መዝገብ ሰብስቡ, ማቴ. ፮፥፲፱–፳፩. በዘለአለማዊ ህይወት ሀብቶች ጊዜ ጠራኋችሁ, ት. እና ቃ. ፵፫፥፳፭. የዘለአለም ሀብትም ለመስጠት የእኔ ናቸው, ት. እና ቃ. ፷፯፥፪ (ት. እና ቃ. ፸፰፥፲፰).