የጥናት እርዳታዎች
ሰማይ


ሰማይ

በቅዱሣት መጻህፍት ውስጥ ሰማይ ሁለት ትርጉሞች አሉት። (፩) እግዚአብሔር የሚኖርበት ቦታ እና የቅዱሳን የወደፊት ቤት (ዘፍጥ. ፳፰፥፲፪መዝ. ፲፩፥፬ማቴ. ፮፥፱)። (፪) ምድርን የሚከብ ሰፊና ገላጣ ቦታ (ዘፍጥ. ፩፥፩፣ ፲፯ዘፀአ. ፳፬፥፲)። ሰማይ በዚህ ምድር ላይ በፅድቅ በመሆን የኖሩ እናም የሞቱ ታማኝ መንፈሶች ለጊዜአዊ የሚገኙበት ቦታ የሆነው ገነት እንዳልሆነ ግልጽ ነው። ኢየሱስ በመስቀል ላይ ከሞተ በኋላ ገነትን ጎበኘ፣ ነገር ግን በሶስተኛው ቀን ወደ አብ ገና እንዳልሄደ ለማርያም ነግሯት ነበር (ሉቃ. ፳፫፥፴፱–፵፬ዮሐ. ፳፥፲፯ት. እና ቃ. ፻፴፰፥፲፩–፴፯)።