ናቡከደነዖር
በብሉይ ኪዳን ውስጥ፣ ይሁዳን ያሸነፈ (፪ ነገሥ. ፳፬፥፩–፬) እና ኢየሩሳሌምን በጦር ሀይል የከበበ (፪ ነገሥ. ፳፬፥፲–፲፩) የባቢሎን ንጉስ። ነቢዩ ሌሂ በ፮፻ ም.ዓ. ንጉስ ናቡከደነዖር ንጉስ ሴዴቅያስንና ህዝቡን በሚወስድበት ጊዜ በምርኮ ወደ ባቢሎን መወሰድን ለማስወገድ ከኢየሩሳሌም እንዲሸሽ ታዘዘ፣ (፩ ኔፊ ፩፥፬–፲፫) (፪ ነገሥ. ፳፭፥፩፣ ፰–፲፮፣ ፳–፳፪) ዳንኤል ናቡከደነዖር ህልምን ተረጎመ (ዳን. ፪፤ ፬)።