የያሬድ ወንድም ደግሞም ያሬዳውያን; ያሬድ ተመልከቱ የመፅሐፈ ሞርሞን ነቢይ እርሱ እና ወንድሙ የህዝብ ቡድንን ከባቢሎን ማማ በምዕራብ ክፍለ አለም ወደሚገኘው የቃል ኪዳን ምድር መርተው በማውጣት የያሬዳውያን ሀገርን መሰረቱ (ኤተር ፩–፮)። ታላቅ እምነት ያለው ሰው ሆኖ ከጌታ ጋር ፊት ለፊት ተነጋገረ (ት. እና ቃ. ፲፯፥፩)። ታሪኩ በመፅሐፈ ኤተር የተመዘገበ ነው። የያሬድ ወንድም ትልቅ እናም ኃያል ሰው በመሆኑ፣ እናም በጌታም በይበልጥ የሚወደድ ነበር, ኤተር ፩፥፴፬. በእምነቱ ምክንያት፣ የያሬድ ወንድም የጌታን ጣት አየ, ኤተር ፫፥፮–፱ (ኤተር ፲፪፥፳). ክርስቶስ የመንፈስ ሰውነቱን ለያሬድ ወንድም አሳየ, ኤተር ፫፥፲፫–፳. ለያሬድ ወንድም ከተገለፀው በላይ የተገለፁ ታላቅ የሆኑ ነገሮች በጭራሽ አልነበሩም, ኤተር ፬፥፬. የያሬድ ወንድም ህዝቡን ስለንጉሳዊ አገዛዝ አስጠነቀቃቸው, ኤተር ፮፥፳፪–፳፫. ጌታ ለያሬድ ወንድም ሁሉንም ነገሮች አሳየው, ኤተር ፲፪፥፳፩. የያሬድ ወንድም በይበልጥ መፃፍ የሚችል ነበር, ኤተር ፲፪፥፳፬. በእምነት የያሬድ ወንድም የዜሪንን ተራራ አንቀሳቀሰ, ኤተር ፲፪፥፴.