መፅሐፈ ኤተር
በንጉስ ሞዛያ ዘመን በሊምሂ ሰዎች ከተገኙት ከሃያ አራቱ ሠሌዳዎች ላይ የተወሰደ የያሬዳውያን ታሪክ።
ምዕራፍ ፩
ሞሮኒ የኤተርን ፅሁፍ አሳጠረ—የኤተር የትውልድ ሐረግ ተዘርዝሯል—በባቢሎናውያን ግንብ ወቅት የያሬዳውያን ቋንቋ አልተቀላቀለም—ጌታ ወደ ተመረጠች ምድር እንደሚመራቸው እናም ታላቅ ሀገርም እንደሚያደርጋቸው ቃል ገብቷል።
፩ እናም እንግዲህ፣ እኔ ሞሮኒ፣ ከዚህች ሃገር ከሰሜን በኩል በጌታ እጅ ጠፍተው የነበሩትን የጥንት ሰዎች ታሪክ መስጠቴን እቀጥላለሁ።
፪ እናም መፅሐፈ ኤተር ከተባለው በሌምሂ ሰዎች ከተገኘው ከሃያ አራተኛው ሠሌዳ ላይ የራሴን ዘገባ እወስዳለሁ።
፫ እናም ስለዓለም መፈጠር የሚያወራው፣ እናም ደግሞ ስለአዳም፣ እናም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እስከ ታላቁ ግንብ ድረስ ያለው ታሪክ፣ እናም እስከዚያም ጊዜ ድረስ በሰው ልጆች መካከል የሆኑት ማናቸውንም ነገሮች የያዘው የዚህ መዝገብ የመጀመሪያ ክፍል እኔ እንደምገምተው በአይሁዶች መካከል ይገኛል—
፬ ስለዚህ ከአዳም ዘመን ጀምሮ እስከዚያን ጊዜ የተከናወኑትን ነገሮች አልፅፍም፤ ነገር ግን በሰሌዳዎቹ ላይ አሉ፤ እናም እነርሱን ያገኘ ታሪኩን በሙሉ ያውቅ ዘንድ ኃይል ይኖረዋል።
፭ ነገር ግን እነሆ፣ እኔ ታሪኩን በሙሉ አልናገርም፣ ነገር ግን ከግንብ ጀምሮ እስከጠፉበት ጊዜ ድረስ ያለውን የታሪክ ክፍል ብቻ እሰጣለሁ።
፮ እናም በዚህ መንገድ ዘገባውን እሰጣለሁ። ይህንን ታሪክ የፃፈው ኤተር ነበር፣ እናም እርሱም የቆሪያንቶር ወገን ነበር።
፯ ቆሪያንቶር የሞሮን ልጅ ነበር።
፰ እና ሞሮንም የኤተም ልጅ ነበር።
፱ እናም ኤተም የአሃህ ልጅ ነበር።
፲ አሃህ የሴት ልጅ ነበር።
፲፩ እና ሴት የሺብሎን ልጅ ነበር።
፲፪ እና ሺብሎን የቆም ልጅ ነበር።
፲፫ እና ቆም የቆሪያንቱም ልጅ ነበር።
፲፬ እና ቆሪያንቱምም የአምኒጋዳ ልጅ ነበር።
፲፭ እና አምኒጋዳ የአሮን ልጅ ነበር።
፲፮ እና አሮን የሔርቶም ልጅ የነበረው የሔት ወገን ነበር።
፲፯ እና ሔርቶም የሊብ ልጅ ነበር።
፲፰ እና ሊብ የኪሽ ልጅ ነበር።
፲፱ እና ኪሽም የቆሮም ልጅ ነበር።
፳ ቆሮም የሌዊ ልጅ ነበር።
፳፩ እና ሌዊ የቂም ልጅ ነበር።
፳፪ እና ቂም የሞሪያንተን ልጅ ነበር።
፳፫ እና ሞሪያንተን የሪፕላኪሽ ወገን ነበር።
፳፬ እና ሪፕላኪሽ የሼዝ ልጅ ነበር።
፳፭ እና ሼዝ የሔት ልጅ ነበር።
፳፮ እና ሔት የቆም ልጅ ነበር።
፳፯ እና ቆም የቆሪያንቱም ልጅ ነበር።
፳፰ እና ቆሪያንቱም የኤመር ልጅ ነበር።
፳፱ እና ኤመር የኦመር ልጅ ነበር።
፴ እና ኦመር የሹል ልጅ ነበር።
፴፩ እና ሹል የቂብ ልጅ ነበር።
፴፪ እናም ቂብም የያሬድ ልጅ የነበረው የኦሪያ ልጅ ነበር።
፴፫ ጌታ የህዝቡን ቋንቋ በቀላቀለበት እናም በምድሪቱ ገፅ ሁሉ ላይም እንዲሠራጩ በቁጣው በማለ ጊዜ ከታላቁ ግንብ ያሬድ ከወንድሞቹ፣ እናም ከቤተሰቦቹ ጋር በመሆን ከሌሎች እና ከቤታሰቦቻቸው ጋር መጣ፣ እናም እንደጌታ ቃልም ህዝቡ ተበትኖ ነበር።
፴፬ እናም የያሬድ ወንድም ትልቅ እናም ኃያል ሰው በመሆኑ፣ እናም በጌታም በይበልጥ የሚወደድ በመሆኑ፣ ያሬድ ወንድሙም እንዲህ ሲል ተናገረው፥ የተናገርነውንም እንዳንረዳ እርሱ የምንናገረውን እንዳይቀላቅልብን ወደ ጌታ ጩህ።
፴፭ እናም እንዲህ ሆነ የያሬድ ወንድም ወደ ጌታ ጮኸ፣ እናም ጌታም ለያሬድ አዘነለት፤ ስለዚህ የያሬድን ቋንቋ አልቀላቀለበትም፤ እናም የያሬድና የወንድሙ ቋንቋ አልተቀላቀለባቸውም።
፴፮ ከዚያም ያሬድ ለወንድሙ እንዲህ አለ፥ እናም ከወዳጆቻችንም ላይ ቁጣውን ይመልስ ዘንድ ቋንቋቸውን እንዳይቀላቅልባቸው በድጋሚ ወደ ጌታ ጩህ።
፴፯ እናም እንዲህ ሆነ የያሬድ ወንድም ወደ ጌታ ጮኸ፣ እናም ጌታ ለወዳጆቹ እናም ደግሞ ለቤተሰቦቹ ራራላቸው፣ ስለዚህ ቋንቋቸውን አልቀላቀለባቸውም።
፴፰ እናም እንዲህ ሆነ ያሬድ ለወንድሙ በድጋሚ እንዲህ ሲል ተናገረ፥ ሂድ እናም ጌታ ከምድሪቱ ወዴት እንደሚያስወጣን ጠይቀው፤ እናም ከምድሪቱ የሚያስወጣን ከሆነ ወዴት መሄድ እንዳለብን ወደ እርሱ ጩህ። እናም ምናልባት ከምድር ሁሉ ወደ ተመረጠችው ስፍራ ጌታ እንደሚወስደን ማን ያውቃል? እናም እንደዚያ የሚሆን ቢሆን ለውርሳችን እንቀበለው ዘንድ ለጌታ ታማኞች እንሁን።
፴፱ እናም እንዲህ ሆነ በያሬድ አንደበት በተነገረው መሰረት የያሬድ ወንድም ወደ ጌታ ጮኸ።
፵ እናም እንዲህ ሆነ ጌታ የያሬድን ወንድም ሰማው፣ እናም ለእርሱም አዘነለት፣ እናም እንዲህ ሲል ተናገረው፥
፵፩ ሂድ እናም መንጋዎቻችሁን ሴት እናም ወንድ የሆኑትን ከሁሉም ዓይነት በአንድ ላይ ሰብስብ፤ እናም ደግሞ በምድር ላይ ካሉት ዘር ፍሬዎች ከሁሉም ዓይነት ያሉትን፤ እናም ቤታሰቦችህን፤ እናም ደግሞ ወንድምህን ያሬድ እና ቤተሰቡን፤ እናም ደግሞ ወዳጆችህን እና ቤተሰቦቻቸውን፣ እናም የያሬድን ወዳጆች እናም ቤተሰቦች በሙሉ በአንድነት ሰብስብ።
፵፪ እናም ይህንን በምታደርግበት ጊዜ ከፊታቸው በመሆን በስተሰሜን ወዳለው ሸለቆ አብረሃቸው ትጓዛለህ። እናም እዚያ ቦታም አገኝሀለሁ፣ እናም ከምድሪቱ ሁሉ በላይ ወደ ተመረጠችው ስፍራም በምትሄድበትም ጊዜ ከፊትህ እሄዳለሁ።
፵፫ እናም እዚያ አንተንና ዘሮችህን እባርካለሁ፣ እናም ከዘሮችህም፣ እናም ከወንድምህ ዘር፣ እናም ከአንተ ጋር ከሚሄዱትም፣ ለራሴ ታላቅ ሀገር አስነሳለሁ። እናም ከምድር ገፅ ላይ ሁሉ ከአንተ ዘር ለራሴ ካበዛኋቸው የበለጠ ታላቅ ሀገር አይኖርም። እናም ይህንንም አደርግልሃለሁ ምክንያቱም ለነዚህ ለረጅም ጊዜያት ወደ እኔ ስለጮህክ ነው።