ቅዱሳት መጻህፍት
ኤተር ፯


ምዕራፍ ፯

ኦሪያ በፅድቅ ነገሰ—ያለአግባብ ሥልጣንን በመያዝና በፀብ መካከል ተቃዋሚዎቹ የሹል እናም የቆሖር መንግስታት ተመሰረቱ—ነቢያት የህዝቡን ክፋትና ጣኦት አምላኪነት ኮነኑ፣ ከዚያም ንሰሃ ገቡ።

እናም እንዲህ ሆነ ኦሪያ በዘመኑ ሁሉ በፅድቅ በምድሪቱ ላይ ፍርድን ፈፅሟል፤ ዘመኑም እጅግ ብዙ ነበር።

እናም ወንዶች እና ሴቶች ልጆችንም ወለደ፤ አዎን፣ ሠላሳ አንድ ልጆችን ወለደ፤ ከእነርሱ መካከል ሃያ ሦስቱ ወንዶች ልጆች ነበሩ።

እናም እንዲህ ሆነ እርሱም ደግሞ በእርጅናው ጊዜ ቂብን ወለደ። እናም እንዲህ ሆነ ቂብም በእርሱ ቦታ ነገሰ፤ እናም ቂብ ቆሪሆርን ወለደ።

እናም ቆሪሆርም ሠላሳ ሁለት ዓመት በሞላው ጊዜ በአባቱ ላይ አመፀ፣ እናም ሄደ እናም በኔሆር ምድር ተቀመጠ፤ እናም እርሱም ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ፣ እናም እነርሱም እጅግ ያማሩ ሆኑ፤ ስለዚህ ቆሪሆርንም ብዙ ሰዎች እንዲከተሉት ወደ እርሱ ሳበ።

እናም ሠራዊቱን በሰበሰበ ጊዜም ንጉሱ ወደሚኖርበት ወደ ሞሮን ምድር መጣ፣ እናም ምርኮኛ አድርገው ወሰዱት፣ ይህም የያሬድ ወንድም እነርሱ ምርኮኛ ይሆናሉ ያለው ይፈፀም ዘንድ ሆነ።

ንጉሱ የተቀመጠበት የሞሮን ምድር በኔፋውያን የወደመች ተብላ ከምትጠራው ምድር አጠገብ ነበረች።

እናም እንዲህ ሆነ ቂብም በጣም እስከሚያረጅ ድረስ ቂብ እናም ህዝቡ በቆሪሆር በልጁ ስር በምርኮ ተቀምጠው ኖሩ፤ ይሁን እንጂ ቂብም በምርኮ በነበረበት ወቅት በእርጅናው ሹልን ወለደ።

እናም እንዲህ ሆነ ሹልም በወንድሙ ተቆጥቶ ነበር፣ እናም ሹልም በረታ እናም በሰው ሀይልም ጠንክሮ ኃያል ሆነ፤ እናም በፍርዱም እንዲሁ ኃያል ነበር።

ስለዚህ ወደ ኤፍሬም ኮረብታ ወጣ፣ እናም ከኮረብታው ብረት አቅልጦ አወጣ፣ እናም ከእርሱ ጋር ለሄዱትም ከብረቱ ጎራዴን ሰራላቸው፤ እናም በጎራዴም ካስታጠቃቸው በኋላ ወደ ኔሆር ከተማ ተመለሰ፣ እናም ከወንድሙ ቆሪሆር ጋር ተዋጋ፣ በዚህም መንገድ መንግስቱን አገኘ እናም ለአባቱ ቂብም መለሰለት።

እናም እንግዲህ ሹል ባደረገው ነገር ምክንያት አባቱ መንግስቱን ለእርሱ ሰጠው፤ ስለዚህ በአባቱ ምትክም መንገስ ጀመረ።

፲፩ እናም እንዲህ ሆነ ሹልም በፅድቅ ፍርድን ይፈጽም ነበር፤ እናም ህዝቡም በቁጥር እጅግ ብዙ በመሆናቸው በምድሪቱ ሁሉ ላይ አገዛዙን አስፋፋ።

፲፪ እናም እንዲህ ሆነ ሹልም ደግሞ ብዙ ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ።

፲፫ እናም ቆሪሆርም ለሰራቸው ብዙ ክፋቶች ንሰሃ ገባ፤ ስለዚህ ሹልም በመንግስቱ ሥልጣንን ሰጠው።

፲፬ እናም እንዲህ ሆነ ቆሪሆርም ብዙ ወንዶችና ሴቶች ልጆች ነበሩት። እናም ከቆሪሆር ወንድ ልጆች መካከልም አንዱ ኖህ የሚባል ነበር።

፲፭ እናም እንዲህ ሆነ ኖህም በንጉሱ በሹል፣ እናም ደግሞ በአባቱ ቆሪሆር ላይ አመፀ፤ ወንድሙ ቆሆርን፣ እናም ደግሞ ወንድሞቹን ሁሉ እናም ብዙ ሰዎችን ወደራሱ ሳበ።

፲፮ እናም ኖህም ከንጉሱ ሹል ጋር ተዋጋ፤ እናም በመጀመሪያ የትውልድ ቦታቸው የነበረውን አገኘ፤ እናም በዚያም የምድሪቱ ክፍል ላይ ንጉስ ሆነ።

፲፯ እናም እንዲህ ሆነ በድጋሚም ከንጉሱ ከሹል ጋር ተዋጋ፤ እናም ንጉስ ሹልን ወሰደ፣ እናም ወደ ሞሮን ምርኮኛ አድርጎ ወሰደው።

፲፰ እናም እንዲህ ሆነ ኖህም ሊገድለው በተዘጋጀ ጊዜ የሹል ልጆች በምሽት አድፍጠው ወደ ኖህ ቤት ገብተው ገደሉት፣ እናም የወህኒ ቤቱን በር ሰበሩ እናም አባታቸውን አወጡት፣ እናም በራሱ መንግስትም በዙፋኑ ላይ መልሰው አስቀመጡት።

፲፱ ስለዚህ፣ የኖህም ልጅ በእርሱ ምትክ መንግስቱን ገነባ፤ ይሁን እንጂ በንጉስ ሹል ላይ ከዚያ በኋላ ኃይልን አላገኙም፤ እናም በንጉስ ሹል አገዛዝ ሥር የነበሩ ሕዝቦች እጅግ በለፀጉ እናም በኃይል ጠነከሩ።

እናም ሀገሩም ተከፋፈለ፤ እናም ሁለት መንግስት ነበሩ፣ የሹል መንግስት እናም የኖህ ልጅ የሆነው የቆሆር መንግስት።

፳፩ እናም የኖህ ልጅ ቆሆር ህዝቡም ከሹል ጋር እንዲዋጉ አደረገ፤ በዚያም ሹልም ድልን አገኘ፣ እናም ቆሆርን ገደለው።

፳፪ እናም እንግዲህ ቆሆርም ናምሩድ የሚባል ልጅ ነበረው፤ እናም ናምሩድም የቆሆርን መንግስት ለሹል ሰጠው፣ እናም በሹል አመለካከትም ተወዳጅ ሆነ፤ ስለዚህ ሹል ታላቅ ድጋፍን ሰጠው፤ እናም በሹል መንግስት ውስጥ እንደ ፍላጎቱ አደረገ።

፳፫ እናም ደግሞ በሹል ንግስናም የህዝቡ ክፋትና የጣዖት ማምለክ በምድሪቱ ላይ እርግማን እንደሚያመጣ፤ እናም ህዝቡም ንሰሃ ካልገባ እንደሚጠፉ የሚተነበዩ በህዝቡ መካከል ከጌታ የተላኩ ነቢያት መጡ።

፳፬ እናም እንዲህ ሆነ ህዝቡም ነቢያትን ሰደቡአቸው፣ እናም ተሳለቁባቸው። እናም እንዲህ ሆነ ንጉስ ሹልም ነቢያቱን በተሳደቡት ሁሉ ላይ ፍርድን ፈረደ።

፳፭ እናም በምድሪቱ ሁሉ ላይም በፈለጉበት ቦታ ለመሄድ ለነቢያት ኃይልን ለመስጠት ህጉ በስራ ላይ እንዲውል አደረገ፤ እናም በዚህም የተነሳ ህዝቡ ንሰሃ ገባ።

፳፮ እናም ህዝቡም ለክፋታቸው እና ለጣዖት ማምለካቸው ንሰሃ በመግባታቸው ጌታ አተረፋቸው፤ እናም በድጋሚ በምድሪቱ ላይ መበልጸግ ጀመሩ። እናም እንዲህ ሆነ ሹልም በእርጅናው ሴቶች እናም ወንዶች ልጆችን ወለደ።

፳፯ እናም በሹል ዘመን ምንም አይነት ተጨማሪ ጦርነት አልነበረም፤ እናም ጌታም ወደ ቃል ኪዳኗ ምድር ጥልቅ የነበረውን ታላቅ ባህር በማሳለፍ ለአባቶቹ ያደረገውን ታላቅ ነገር አስታወሰ፤ ስለዚህ በዘመኑ ሁሉ በፅድቅ ፍርድን አከናወነ።