ቅዱሳት መጻህፍት
ኤተር ፮


ምዕራፍ ፮

የያሬዳውያን ጀልባዎች በነፋሱ ወደ ቃል ኪዳን ምድር ተወሰዱ—ህዝቡም ጌታ ቸር በመሆኑ አወደሱት—ኦሪያም በእነርሱ ላይ ንጉስ እንዲሆን ተሾመ—ያሬድና ወንድሙ ሞቱ።

እናም እንግዲህ፣ እኔ ሞሮኒ፣ የያሬድን እና የወንድሙን ዘገባ መስጠቴን እቀጥላለሁ።

እናም እንዲህ ሆነ የያሬድ ወንድም ወደ ተራራው ተሸክሞ የወሰዳቸውን ድንጋዮች ጌታ ካዘጋጃቸው በኋላ፣ የያሬድ ወንድም ከተራራው ላይ ወረደ፣ እናም ድንጋዮቹን በጀልባዎች ውስጥ እያንዳንዱን በጫፉ ላይ አስቀመጠው፤ እናም እነሆ፣ ድንጋዮቹም ለመርከቡ ብርሃን ሰጡ።

እናም ታላቁንም ውሃ በጨለማ እንዳያቋርጡ ዘንድ ጌታ ድንጋዮቹን ለወንዶች፣ ለሴቶች እና ለህፃናት ብርሃን እንዲሰጡ በጨለማም እንዲያበሩ አደረገ።

በውኃ ላይ በሚቆዩበት ጊዜ የሚኖሩበት የተለያዩ የምግብ ዓይነቶችን አዘጋጅተው ነበር፣ እናም ደግሞ ለበጎቻቸው፣ እናም ለመንጋዎቻቸው፣ እናም ለያዙአቸው አራዊቶች ወይም እንስሳቶች፣ ወይም ወፎች ሁሉ ምግብ ይዘው ነበር—እናም እንዲህ ሆነ እነዚህን ነገሮች ሁሉ ካደረጉ በኋላ፣ እራሳቸውን ለጌታ ጥበቃ አሳልፈው በመስጠት፣ ወደ ውሀ መጓዣቸው ወይም በጀልባዎቻቸው ሄዱ።

እናም እንዲህ ሆነ ጌታ እግዚአብሔርም ወደ ቃል ኪዳኗ ምድር በሚያመራው በውኃው ገፅ ላይ ኃይለኛ ነፋስ እንዲነፍስ አደረገ፤ እናም ከነፋሱም በፊት በባህሩ ሞገድ ተወስደው ነበር።

እናም እንዲህ ሆነ በእነርሱ ላይ ባረፈው በተራራማው ማዕበል እናም ደግሞ በኃያሉ ነፋስ ምክንያት በመጣው በታላቁና ኃይለኛው አውሎ ነፋስ ብዙ ጊዜ ባህሩ ውስጥ ተቀብረው ነበር።

እናም እንዲህ ሆነ ጀልባዎቻቸው እንደሣህን የጠበቀ ስለነበሩ፣ እናም ደግሞ እንደኖህ መርከብም የጠበቁ ስለነበሩ፣ ወደ ጥልቅ ውሀውም በሚቀበሩበትም ጊዜ የሚጎዳቸው ውኃ አልነበረም፤ ስለዚህ በበርካታ ውኃም በተከበቡም ጊዜ ወደ ጌታ ጮሁ እናም እርሱም በድጋሚ ከብዙ ውሀዎች በላይ አወጣቸው።

እናም እንዲህ ሆነ እነርሱም በውኃው ላይ በነበሩበት ጊዜ ነፋሱ ወደ ቃል ኪዳኗ ምድር መንፈሱን በጭራሽ አላቆመም፤ እናም ከነፋሱ በፊትም እንደዚህ ተገፉ።

እናም ጌታን በዝማሬ ያወድሱት ነበር፤ አዎን፣ የያሬድ ወንድም ጌታን በዝማሬ ያወድሰው ነበር፣ እናም ቀኑን ሙሉ ጌታን ያመሰግነው እናም ያወድሰው ነበር፤ እናም ምሽት በሆነም ጊዜ ጌታን ማወደሳቸውን አላቆሙም ነበር።

እናም በዚሁ ወደ ፊት ሄዱ፤ እናም ምንም የባህር አውሬም ሊሰብራቸው አልቻለም፣ አሳ ነባሪም ሊጎዳቸው አልቻለም፤ እናም በውኃው ከላይ በኩል እንዲሁም ከታችም ቢሆኑም ያለማቋረጥ ብርሃን ነበራቸው።

፲፩ እናም ለሦስት መቶ አርባ አራት ቀናት በውኃው ላይ ይጓዙ ነበር።

፲፪ እናም በቃል ኪዳኗ ምድር ዳርቻም አረፉ። እናም በቃል ኪዳኗ ምድር እግራቸውን ባሳረፉ ጊዜ በምድሪቷ ላይ እራሳቸውን ዝቅ አደረጉ፣ እናም በጌታ ፊት እራሳቸውን አዋረዱ፣ እና ጌታም በእነርሱ ላይ ምህረቱን ያበዛ በመሆኑ በፊቱ የደስታ እንባቸውን አፈሰሱ።

፲፫ እናም እንዲህ ሆነ በምድሪቱም ላይ ተሰራጩ እናም እርሻ ጀመሩ።

፲፬ እናም ያሬድ አራት ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ እናም እነርሱም ያቆም፤ እናም ጊልጋ፣ እናም ማሃ እናም ኦሪያ ተብለው ይጠሩ ነበር።

፲፭ እናም ደግሞ የያሬድ ወንድም ወንድና ሴት ልጆችን ወለደ።

፲፮ እናም የያሬድ ወዳጆች እናም ወንድሞቹ በቁጥር ሃያ ሁለት ነፍሳት ነበሩ፤ እናም እነርሱ ደግሞ ወደ ቃልኪዳኗ ምድር ከመምጣታቸው በፊት ወንድና ሴት ልጆችን ወልደው ነበር፤ እናም ስለዚህ ብዙ መሆን ጀምረው ነበር።

፲፯ እናም እነርሱም በጌታ ፊት በትህትና መራመድን ተምረው ነበር፤ እናም ከላይ ከሰማይም ደግሞ ተምረው ነበር።

፲፰ እናም እንዲህ ሆነ በምድሪቱ ላይ መስፋፋት፣ እናም መባዛት፣ እናም ምድሪቷን ማረስ ጀመሩ፤ እናም በምድሪቱ ላይ ጠነከሩ።

፲፱ እናም የያሬድ ወንድም አረጀ፣ እናም በቅርቡም ወደ መቃብር መውረድ እንዳለበት ተመለከተ፤ ስለዚህ ለያሬድ እንዲህ ሲል ተናገረው፥ ሕዝባችንን እንድንቆጥር፣ ወደ መቃብራችን ከመውረዳችን በፊት ከእኛ የሚፈልጉትን እናውቅ ዘንድ ህዝቦቻችንን በአንድነት እንሰብስባቸው።

እናም በዚህም መሰረት ህዝቡም በአንድነት ተሰባስቦ ነበር። እንግዲህ የያሬድ ወንድም ወንዶችና ሴቶች ልጆቹ በቁጥር ሃያ ሁለት ነፍሳት ነበሩ፤ እናም የያሬድ ወንዶችና ሴቶች ልጆቹ አስራ ሁለት ነበሩ፤ እናም አራት ወንድ ልጆች ነበሩት።

፳፩ እናም እንዲህ ሆነ ያሬድና ወንድሙም ህዝባቸውን ቆጠሩ፤ እናም ከቆጠሩአቸው በኋላም ወደ መቃብር ከመውረዳቸው በፊት ከእነርሱ የሚፈልጓቸውን ነገሮች ለማወቅ ፈለጉ።

፳፪ እናም እንዲህ ሆነ ህዝቡም የፈለጉት ከልጆቻቸው አንዱን በእነርሱ ላይ ንጉስ አድርገው እንዲቀቡት ነበር።

፳፫ እናም አሁን እነሆ፣ ይህ ለእነርሱ አሳዛኝ ነበር። እናም የያሬድ ወንድም እንዲህ አላቸው፥ በእርግጥ ይህ ነገር ወደ ግዞት ያመራል

፳፬ ነገር ግን ያሬድ ለወንድሙ እንዲህ አለው፥ ንጉስ ይኖራቸው ዘንድ ፍቀድላቸው። እናም ስለዚህ እንዲህ አላቸው፥ ከወንዶች ልጆቻችን እናንተም የፈለጋችሁትን አንድን ንጉስ ምረጡ።

፳፭ እናም እንዲህ ሆነ የያሬድን ወንድም የበኩር ልጁን መረጡ፤ ስሙም ፓጋግ ይባል ነበር። እናም እንዲህ ሆነ እርሱም ንጉሳቸው መሆንን አልተቀበለውም፣ እናም ንጉሳቸው አልሆነም። እናም ህዝቡ አባቱ እንዲገፋፋው ፈለጉ፣ ነገር ግን አባቱ አላስገደደውም፤ እናም እርሱም ማንንም ሰው ንጉስ ሁን ብለው እንዳያስገድዱ አዘዛቸው።

፳፮ እናም እንዲህ ሆነ የፓጋግን ወንድሞች በሙሉ መረጡአቸው፣ እናም እነርሱም ንጉስ ለመሆን አልፈለጉም።

፳፯ እናም እንዲህ ሆነ ከአንዱ በስተቀር የያሬድ ወንድም ልጆች ሁሉም አልፈለጉም፤ እናም ኦሪያ በህዝቡ ላይ ንጉስ ለመሆን ተቀብቶ ነበር።

፳፰ እናም እርሱ መንገስ ጀመረ፣ እናም ህዝቦቹ መበልፀግ ጀመሩ፤ እናም እጅግ ሀብታም ሆኑ።

፳፱ እናም እንዲህ ሆነ ያሬድ እንዲሁም ደግሞ ወንድሙም ሞቱ፤

እናም እንዲህ ሆነ ኦሪያ በጌታ ፊት እራሱን ዝቅ አድርጎ ተራመደ፣ እናም ጌታም ለአባቱ ምን ያህል ድንቅ ነገሮችን እንዳደረገ አስታወሰ፤ እናም ደግሞ ጌታ ለአባቶቻቸው ምን ያህል ታላላቅ ነገሮችን እንዳደረገላቸው ለህዝቡ አስተማራቸው።