መራመድ፣ ከእግዚአብሔር ጋር መራመድ (መሄድ) ደግሞም መንገድ; ታዛዥነት፣ ታዛዥ፣ መታዘዝ; ጻድቅ፣ ጽድቅ ተመልከቱ ከእግዚአብሔር ትምህርቶች ጋር መስማማት ወይም እግዚአብሔር ህዝቦቹ እንዲኖሩ በሚፈልግበት መንገድ መኖር፤ ለመንፈስ ቅዱስ መነሳሳት ተቀባይ መሆን እና ታዛዥ መሆን። በሕጌ ይሄዱ ወይም አይሄዱ እንደሆነ እኔ እንድፈትናቸው, ዘፀአ. ፲፮፥፬. በቅንነት የሚሄዱትን ከመልካም ነገር አያሳጣቸውም, መዝ. ፹፬፥፲፩. በትእዛዜ የሚሄዱ እና ፍርዴን የሚጠብቁ፣ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል, ሕዝ. ፲፩፥፳–፳፩ (ዘዳግ. ፰፥፮). እግዚአብሔርም ከአንተ ዘንድ የሚሻው ምንድር ነው? ከአምላክህም ጋር በትሕትና ትሄድ ዘንድ ነው, ሚክ. ፮፥፰ (ት. እና ቃ. ፲፩፥፲፪). እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን እንሂድ, ፩ ዮሐ. ፩፥፯ (፪ ዮሐ. ፩፥፮; ፫ ዮሐ. ፩፥፬; ፬ ኔፊ ፩፥፲፪). ወደ ህይወት በሚያመራው በቀጭኑ ጎዳና ካልተራመዱ, ፪ ኔፊ ፴፫፥፱. በእግዚአብሔር ፊት በንጹህ ህሊና ተመራመድ, ሞዛያ ፪፥፳፯. በእርሱ ፊት እንከን የሌላችሁ በመሆን ተራመዱ, አልማ ፯፥፳፪. የቤተክርስቲያን አባላት አምላካዊ አካሄድ እና ንግግር ብቁ መሆናቸውን ያሳዩ, ት. እና ቃ. ፳፥፷፱. በነቢዩን አድምጡ እናም ፈቴ በቅድስና ተራመዱ, ት. እና ቃ. ፳፩፥፬. ልጆቻቸውን በጌታ ፊት በቅንነት እንዲራመዱም ያስተምሩ, ት. እና ቃ. ፷፰፥፳፰. አንተም ከእኔ ጋር ሁን፣ እና እኔም ከአንተ ጋር፤ ስለዚህ ከእኔ ጋር ሄድ, ሙሴ ፮፥፴፬.