ሚልክያስ
በ፬፻፴ ም.ዓ. አካባቢ የጻፈና የተነበየ የብሉይ ኪዳን ነቢይ።
ትንቢተ ሚልክያስ
የሚልክያስ መፅሐፍ ወይም ትንቢት የብሉይ ኪዳን የመጨረሻ መፅሐፍ ነው። ይህም የሚቀጥሉት አራት ጭብጥ መልእክቶች ነበሩት፥ (፩) የእስራኤል ኃጢያቶች—ሚልክያስ ፩፥፮–፪፥፲፯፤ ፫፥፰–፱፤ (፪) ታዛዥ ባለመሆናቸው ምክንያት በእስራኤል ላይ የሚመጣው ፍርድ—ሚልክያስ ፩፥፲፬፤ ፪፥፪–፫፣ ፲፪፤ ፫፥፭፤ (፫)፤ ለታዛዥነት ቃል ኪዳን—ሚልክያስ ፫፥፲–፲፪፣ ፲፮–፲፰፤ ፬፥፪–፫፤ እና (፬) እስራኤልን በሚመለከት ትንቢቶች ሚልክያስ ፫፥፩–፭፤ ፬፥፩፣ ፭–፮ (ት. እና ቃ. ፪፤ ፻፳፰፥፲፯፤ ጆ.ስ.—ታ. ፩፥፴፯–፴፱)።
በትንቢቶቹ ውስጥ፣ ሚልክያስ ስለመጥምቁ ዮሐንስ (ሚል. ፫፥፩፤ ማቴ. ፲፩፥፲)፣ ስለአስራት ህግ (ሚል. ፫፥፯–፲፪)፣ ስለጌታ ዳግም ምፅዓት (ሚል. ፬፥፭)፣ እናም ስለኤልያስ መመለስ (ሚል. ፬፥፭–፮፤ ት. እና ቃ. ፪፤ ፻፳፰፥፲፯፤ ጆ.ስ.—ታ. ፩፥፴፯–፴፱) ጻፈ። አዳኝ የሚልክያስን ምዕራፍ ፫ እና ፬ ለኔፋውያን ጠቀሰ (፫ ኔፊ ፳፬–፳፭)።