ማሳደድ፣ መሳደድ ደግሞም ጭንቀት ተመልከቱ ሌሎችን በእምነታቸው ወይም በማህበራዊ ሁኔታቸው ምክንያት ሌሎችን ማስጨነቅ ወይም ማሳዘን፤ ማስፈራራት ወይም መጨቆን። ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው, ማቴ. ፭፥፲ (፫ ኔፊ ፲፪፥፲). ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ, ማቴ. ፭፥፵፬ (፫ ኔፊ ፲፪፥፵፬). ሀብታም በመሆናቸው፣ ትሁቶችን ያሳድዳሉ, ፪ ኔፊ ፱፥፴ (፪ ኔፊ ፳፰፥፲፪–፲፫). የስደት መከራ ቢደርስባቸውም ክርስቶስን ወደ ፊት የሚመለከቱ ጻድቃኖች የማይጠፉት ናቸው, ፪ ኔፊ ፳፮፥፰. እነዚህ ነገሮች ሁሉ ለአንተ ልምድ ይሰጡሀል, ት. እና ቃ. ፻፳፪፥፯.