የጥናት እርዳታዎች
መፅሐፈ ሞርሞን


መፅሐፈ ሞርሞን

በየኋለኛው ቀን ቅዱስና የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስትያን ተቀባይ ከሆኑት አራት የቅዱስም መጻህፍት ጥራዞች አንዱ። ይህም የአሜሪካዎች የጥንት ነዋሪዎች መዝገቦች ሞርሞን ተብሎ በሚጠራው በጥንት ነቢይ የታጠረ ነው። የተጻፈውም ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደሆነ ለመምስከር ነበር። ይህን መዝገብ በሚመለከት ይህን በእግዚአብሔር ስጦታ እና ሀይል የተረጎመው ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ለወንድሞች መጽሐፈ ሞርሞን በምድር ካሉ መጽሐፍት በሙሉ የበለጠ ትክክል እንደሆነ፣ እናም የኃይማኖታችን የማዕዘን ድንጋይ እንደሆነና ከማንኛውም ሌላም መጽሐፍ በበለጠ በውስጡ ባሉት አስተያየቶች በመኖር ሰው ወደ እግዚአብሔር ሊቀርብ እንደሚችል ነገርኳቸው ብሏል (በመፅሐፈ ሞርሞን መጀመሪያ ያለውን መግቢያ ተመልከቱ)።

መፅሐፈ ሞርሞን ከጥንቱ አለም ወደ አሜሪካ ክፍለ አህጉሮች የሄዱት የሶስት ቡድኖች ሀይማኖታዊ መዝገብ ነው። እነዚህ ቡድኖች የሀይማኖታቸውን እና የአለማዊ ታሪኮቻቸውን በብረት ሰሌዳዎች ላይ በጻፉ ነቢያት ይመሩ ነበር። መፅሐፈ ሞርሞን ከትንሳኤው በኋላ ኢየሱስ ክርስቶስ በአሜሪካዎች ውስጥ የሚገኙትን ህዝቦች እንደጎበኘ መዝግቧል። የክርስቶስን ጉብኝት የሁለት መቶ አመት ሰላም ዘመን ተከተለ።

ከኔፋውያን ነቢያት የመጨረሻው ሞሮኒ የእነዚህ ህዝቦችን የታጠሩ መዝገቦችን ዘጋ እና በ፬፻፳፩ ዓ.ም. አካባቢ ደበቃቸው። በ፲፰፻፳፫ (እ.አ.አ.)፣ ከሞት የተነሳው ሞሮኒ ጆሴፍ ስሚዝን ጎበኘ እና በኋላም እነዚህን ጥንታዊ እና ቅዱስ መዝገቦች እንዲተረጎሙ እና እንደ ሌላኛው የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክርነት እንዲመጡ ሰጠው።