ዘይት ደግሞም ለታመሙት አገልግሎት መስጠት; መቀባት; የወይራ ዛፍ ተመልከቱ በቅዱሣት መጻህፍት ውስጥ ዘይት ሲጠቀስ፣ ብዙ ጊዜ የወይራ ዛፍ ዘይት ማለት ነው። ከብሉይ ኪዳን ዘመናት ጀምሮ፣ የወይራ ዛፍ ዘይት ለቤተመቅደስ እና ለድንኳን ስርዓት፣ ፋኖስ ለማብራት፣ እና ለምግብ የሚጠቀሙበት ነው። የወይራ ዘይት አንዳንዴ ለንጹህነት እና ለመንፈስ ቅዱስና ለእርሱ ተጽዕኖ ምልክት ነው (፩ ሳሙ. ፲፥፩፣ ፮፤ ፲፮፥፲፫፤ ኢሳ. ፷፩፥፩–፫)። ካህኑም በእጁ ውስጥ ካለው ዘይት የሚነጻውን ሰው የቀኝ ጆሮውን ጫፍ ላይ ያስነካዋል, ዘሌዋ. ፲፬፥፳፰–፳፱. በሕዝቡ በእስራኤል ላይ ንጉሥ እንድትሆን እቀባህ ዘንድ እግዚአብሔር ላከኝ, ፩ ሳሙ. ፲፭፥፩. ዘይቱም ከባልቴቷ ማሰሮው አልጎደለም, ፩ ነገሥ. ፲፯፥፲–፲፮. ጌታ ራሴን በዘይት ቀባህ, መዝ. ፳፫፥፭. ብዙ ድውዮችንም ዘይት ቀቡ, ማር. ፮፥፲፫. ሽምግሌዎች እርሱን ዘይት ቀብተው ይጸልዩለት, ያዕ. ፭፥፲፫–፲፭. መብራታችሁን አስተካክላችሁ ለኩሱ እና ዘይታችሁን ያዙ, ት. እና ቃ. ፴፫፥፲፯ (ማቴ. ፳፭፥፩–፲፫).