ጻድቅ፣ ጽድቅ ደግሞም መራመድ፣ ከእግዚአብሔር ጋር መራመድ (መሄድ); ቅንነት; ብቁ፣ ብቁነት; ኃጢያተኛ፣ አመፃ; የእግዚአብሔር ትእዛዛት ተመልከቱ ጻድቅ፣ ቅዱስ፣ ምግባረ ጥሩ፣ ቅን መሆን፤ ለእግዚአብሔር ትእዛዛት ታዛዥ በመሆን መስራት፤ ኃጢያትን ማስወገድ። ጌታ ጻድቅን ይባርካል, መዝ. ፭፥፲፪. የእግዚአብሔር ዓይኖች ወደ ጻድቃን ናቸው, መዝ. ፴፬፥፲፭፣ ፲፯ (፩ ጴጥ. ፫፥፲፪). ጻድቃን በበዙ ጊዜ ሕዝብ ደስ ይለዋል, ምሳ. ፳፱፥፪ (ት. እና ቃ. ፺፰፥፱–፲). ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው, ማቴ. ፭፥፮ (፫ ኔፊ ፲፪፥፮). አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ, ማቴ. ፮፥፴፫. ጻድቃን ግን ወደ ዘላለም ሕይወት ይሄዳሉ, ማቴ. ፳፭፥፵፮. የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች, ያዕ. ፭፥፲፮. ፃድቅ የሆነ በእግዚአብሔር የተወደደ ነው, ፩ ኔፊ ፲፯፥፴፭. ፃድቃንን ይጠብቃል፣ መፍራት የለባቸውም, ፩ ኔፊ ፳፪፥፲፯፣ ፳፪. በህዝቦቹ ፅድቅ ምክንያት ሰይጣን ኃይል የለውም, ፩ ኔፊ ፳፪፥፳፮. ፅድቅ ከሌለ ደስታም የለም, ፪ ኔፊ ፪፥፲፫. ፃድቃን የእግዚአብሔርን መንግስት ይወርሳሉ, ፪ ኔፊ ፱፥፲፰. የእውነት ቃላት ጻድቆች አይፈሯቸውም, ፪ ኔፊ ፱፥፵. ሰዎች ሁሉ ወደ ፃድቁ መንገድ ይለወጣሉ, ሞዛያ ፳፯፥፳፭–፳፮. የፃድቃኖች ስም በህይወት መፅሐፍ ይፃፋል, አልማ ፭፥፶፰. የፅድቅ ተፈጥሮ ተቃራኒ በሆነው ነገር ክፋትን በመስራት ደስታን ተመኝታችኋል, ሔለ. ፲፫፥፴፰. የጻድቅን መዝሙር ለእኔ ጸሎት ነው, ት. እና ቃ. ፳፭፥፲፪. የጽድቅንም ጥሩር ለብሳችሁ ቁሙ, ት. እና ቃ. ፳፯፥፲፮ (ኤፌ. ፮፥፲፬). ለእነሱም የጻድቃን መሞት ጣፋጭ ትሆናለች, ት. እና ቃ. ፵፪፥፵፮. ጻድቆች ከእያንዳንዱ ሀገሮች ተሰብሰበው ይወጣሉ, ት. እና ቃ. ፵፭፥፸፩. ሰዎች ጥሩ ስራን ብዙ ጻድቅነቶችን በራሳቸው ነጻ ፈቃድ መስራት አለባቸው, ት. እና ቃ. ፶፰፥፳፯. የጻድቅ ስራ የሚሰራው በዚህ አለም ሰላም እና በወዲያኛው አለምም ዘለአለማዊ ህይወትን ይቀበላል, ት. እና ቃ. ፶፱፥፳፫. በዳግም ምፅዓት፣ ጻድቅ እና ክፉዎች በሙሉ ይለያያሉ, ት. እና ቃ. ፷፫፥፶፬. የሰማይ ሀይሎች በጽድቅ መሰረታዊ መርሆች ብቻ የሚካሄድ ነው, ት. እና ቃ. ፻፳፩፥፴፮. በጻድቃን መካከል ሰላም ነበር, ት. እና ቃ. ፻፴፰፥፳፪. የፅዮን ህዝብ በጽድቅ ኖሩ, ሙሴ ፯፥፲፰. አብርሐም የጽድቅ ተከታይ ነበር, አብር. ፩፥፪.