አማላጅ ደግሞም ኢየሱስ ክርስቶስ; የኃጢያት ዋጋን መክፈል፣ የኃጢያት ክፍያ ተመልከቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ከአብ ጋር አማላጃችን ነው (ሞሮኒ ፯፥፳፰) እና ከእርሱም ጋር ምክንያታችንን ይለምንልናል፥ የሚማለድ ወይም መካከለኛ። ኢየሱስ ክርስቶስ በሰው እና በእግዚአብሔር መካከል የሚማለድ ነበር። የእርሱ የኃጢያት ክፍያ ሰዎች ለኃጢያታቸው ንስሀ ለመግባት እና ከእግዚአብሔር ጋር ለመታረቅ የሚቻልበት መንገድ ሰራ። በኢየሱስ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም, ዮሐ. ፲፬፥፮. በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ, ፩ ጢሞ. ፪፥፭. ክርስቶስ በኪዳን ደግሞ መካከለኛ እንደሚሆን በዚያ ልክ እጅግ የሚሻል ነው, ዕብ. ፰፥፮ (ዕብ. ፱፥፲፭; ፲፪፥፳፬; ት. እና ቃ. ፻፯፥፲፱). ኢየሱስ ክርስቶስ ከአብ ዘንድ አማላጃችን ነው, ፩ ዮሐ. ፪፥፩ (ት. እና ቃ. ፻፲፥፬). ኢየሱስ ለሰው ልጆች ሁሉ ይማለዳል, ፪ ኔፊ ፪፥፱ (ዕብ. ፯፥፳፭). ቅዱሱ መሲህ ለሰው ልጆች ሁሉ ያማልዳል, ፪ ኔፊ ፪፥፱ (ኢሳ. ፶፫፥፲፪; ሞዛያ ፲፬፥፲፪). በታላቁ አማላጅ ተመኩ, ፪ ኔፊ ፪፥፳፯–፳፰. ኢየሱስ በሞት ላይ ድልን አገኘ፤ ለሰው ልጆች እንዲማልድ ኃይልን ሰጠው, ሞዛያ ፲፭፥፰. ከአብ ዘንድ አማላጃችሁ ነኝ, ት. እና ቃ. ፳፱፥፭. ኢየሱስ ክርስቶስ ምክንያታችሁን ይማጸንላችኋል, ት. እና ቃ. ፵፭፥፫–፭. የአዲስ ኪዳን አማላጅ በሆነው ኢየሱስ ፍጹም ሆነናል, ት. እና ቃ. ፸፮፥፷፱.