የጥናት እርዳታዎች
ወደ ቆሮንቶስ መልእክት


ወደ ቆሮንቶስ መልእክት

በአዲስ ኪዳን ውስጥ ሁለት መፅሐፎች። እነዚህ ጳውሎስ በቆሮንቶስ ለሚገኙት ቅዱሳን በመካከላቸው ያለውን ረብሻ ለማስተካከል የጻፈው ደብዳቤዎች ነበሩ። ቆሮንቶስ የኖሩት ክፉ በሆኑ ህብረተሰቦች ውስጥ ነበር።

መጀመሪያይቱ ቆሮንቶስ

ምዕራፍ ፩ የጳውሎስን ሰላምታና አንድ ስለመሆን የገሰጸባቸውን ይይዛል። ምዕራፍ ፪–፮ የቆሮንቶስ ቅዱሳን ስህተት ጳውሎስ ያስተካከላቸው ናቸው። ምዕራፍ ፯–፲፪ለአንዳንድ ጥያቄዎች የጳውሎስን መልስ የያዙ ናቸው። ምዕራፍ ፲፫–፲፭ በልግስና፣ በመንፈሳዊ ስጦታዎች፣ እና በትንሳኤ ላይ ያተኮሩ ናቸው። ምዕራፍ ፲፮ በእምነት ጠንክረው እንዲቆሙ የጳውሎስን ምክር የያዙ ናቸው።

ሁለተኛይቱ ቆሮንቶስ

ምዕራፍ ፩ የጳውሎስን ሰላምታና የመጽናናት መልእክት ይይዛል። ምዕራፍ ፪ ለቲቶ የግል ምክርን የያዘ ነው። ምዕራፍ ፫–፯ ወንጌል በቅዱሳንና በመሪዎቻቸው ህይወቶች ውስጥ ስላለው ሀይል ይናገራሉ። ምዕራፍ ፰–፱ ቅዱሳንን ለደሀዎች በደስታ እንዲሰጡ ይመክራሉ። ምዕራፍ ፲–፲፪ ጳውሎስ ስለሐዋሪያነቱ የሚናገርባቸው ናቸው። ምዕራፍ ፲፫ ፍጹም ስለመሆን በትህትና የሚያስጠነቅቅ ነው።