መጀመሪያ ደግሞም መፍጠር፣ ፍጥረት; ቅድመ ምድራዊ ህይወት; ኢየሱስ ክርስቶስ ተመልከቱ በአጠቃላይ ስለ ስጋዊ ህይወት—ይህም ማለት ስለቅድመ ምድራዊ ህይወት ይናገራል። አንዳንዴ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ መጀመሪያ ይጠቀሳል። በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ, ዘፍጥ. ፩፥፩ (ሙሴ ፪፥፩). በመጀመሪያው ቃል ነበረ, ዮሐ. ፩፥፩. እኔ አለፋና ኦሜጋ፣ የመጀመሪያው እና የመጨረሻው ነኝ, ፫ ኔፊ ፱፥፲፰. ክርስቶስ መጀመሪያው እና መጨረሻው ነው, ት. እና ቃ. ፲፱፥፩. አዲሱ እና ዘለአለማዊው ቃል ኪዳን ከመጀመሪያው ጀምሮ ነበር, ት. እና ቃ. ፳፪፥፩. ሰው በመጀመሪያም ከሰው ጋር ነበር, ት. እና ቃ. ፺፫፥፳፫፣ ፳፱. የተከበሩና ታላቅ መንፈሳት ከመጀመሪያም መሪዎች እንዲሆኑ ተመርጠው ነበር, ት. እና ቃ. ፻፴፰፥፶፭. አንድያ ልጄ ከመጀመሪያ ጀምሮ ከእኔ ጋር ነበር, ሙሴ ፪፥፳፮.