የኖኅ ዘመን የጥፋት ውሀ ደግሞም መርከብ; ቀስተ ዳመና; ኖኅ፣ የመፅሐፍ ቅዱስ የአባቶች አለቃ ተመልከቱ በኖህ ዘመን ምድር በሙሉ በውሀ ሰምጣ ነበር። ይህም የምድር ጥምቀትና ጽዳት ምሳሌ ነበር (፩ ጴጥ. ፫፥፳–፳፩)። እግዚአብሔር ሥጋን ሁሉ ለማጥፋት በምድር ላይ የጥፋት ውኃን ያመጣል, ዘፍጥ. ፮፥፲፯ (ሙሴ ፯፥፴፬፣ ፵፫፣ ፶–፶፪; ፰፥፲፯፣ ፴). ከሰባት ቀንም በኋላ የጥፋት ውኃ በምድር ላይ ሆነ, ዘፍጥ. ፯፥፲. እግዚአብሔር ቀስቱን በደመና ላይ እንደ ቃል ኪዳን ምልክት አስቀመጠ, ዘፍጥ. ፱፥፱–፲፯. ውኃውም ከምድሪቱ ገፅ ከሸሸ በኋላ የአሜሪካ መሬት ከሁሉም መሬት በላይ የተመረጠች ምድር ሆነች, ኤተር ፲፫፥፪. ክፉው በጥፋት ውሀ ይሞታል, ሙሴ ፯፥፴፰፤ ፰፥፳፬.