ማተም፣ ማስተሳሰር ደግሞም ስነስርዓቶች; ኤልያስ; ክህነት ተመልከቱ በሰማይ በምድር ላይ በክህነት ስልጣን የተከናወኑትን ስነስርዓቶች ማረጋገጥ። ስነስርዓቶች የሚታተሙት ቅዱስ የተስፋ መንፈስ በሆነው መንፈስ ቅዱስ ተቀባይነትን ሲቀበሉ ነው። በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል, ማቴ. ፲፮፥፲፱ (ማቴ. ፲፰፥፲፰; ት. እና ቃ. ፻፳፬፥፺፫; ፻፴፪፥፵፮). በተስፋው መንፈስ በመንፈስ ቅዱስ ታተማችሁ, ኤፌ. ፩፥፲፫. በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማይ የታሰረ ይሆን ዘንድ ስልጣን ይኖርሃል, ሔለ. ፲፥፯. ለእነሱ በምድርም ሆነ በሰማይ የማሰር ኃይል ተሰጥቷቸዋል, ት. እና ቃ. ፩፥፰. በሰለስቲያል ክብር ያሉት በቅዱስ የተስፋ መንፈስ ታትመዋል, ት. እና ቃ. ፸፮፥፶–፸. ኤልያስ የማስተሳሰር ሀይል ቁልፎችን ወደ ጆሴፍ ስሚዝ እጆች አሳለፈ, ት. እና ቃ. ፻፲፥፲፫–፲፮. ይህም የሚያትም እና የሚያሳስር ሀይል ነው, ት. እና ቃ. ፻፳፰፥፲፬. ተጨማሪ እርግጠኛ የትንቢት ቃል ማለት ሰው በዘለአለም ህይወት እንደታተመ አውቋል ማለት ነው, ት. እና ቃ. ፻፴፩፥፭. በተቀደሰ ቅዱስ የተስፋ መንፈስ ያልተሰሩ ሰዎች ሲሞቱ መጨረሻ አላቸው, ት. እና ቃ. ፻፴፪፥፯. በቤተመቅደስ የሚደረግ ታላቅ ስራ ልጆችን ከወላጆቻቸው ጋር ማስተሳሰርን ይጨውራል, ት. እና ቃ. ፻፴፰፥፵፯–፵፰.