የክርስቶስ ተቃዋሚ ደግሞም ዲያብሎስ ተመልከቱ የእውነት ወንጌልን የደህንነት አላማ አስመስሎ የሚሰራ እና በግልፅ ወይም በሚስጥር ክርስቶስን የሚቃወም ሰው ወይም ነገር። ገላጩ ዮሐንስ የክርስቶስ ተቃዋሚን እንደ አታላይ ገልጾታል (፩ ዮሐ. ፪፥፲፰–፳፪፤ ፬፥፫–፮፤ ፪ ዮሐ. ፩፥፯)። ታላቁ የክርስቶስ ተቃዋሚ ሉሲፈር ነው፣ ነገር ግን መንፈሳዊ እና ስጋዊ ፍጡር የሆኑ ብዙ ደጋፊዎች አሉት። አምላክ ከተባለው ሁሉ ላይ ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርገው ተቃዋሚ የጥፋት ልጅ, ፪ ተሰ. ፪፥፩–፲፪. ከተሰጡት ምልክቶች የተነሣ በምድር የሚኖሩትን ያስታል, ራዕ. ፲፫፥፲፫–፲፯. ሼረም ክርስቶስን ካደ እናም ብዙዎችን አታለለ, ያዕቆ. ፯፥፩–፳፫. ኔሆር ሀሰተኛ ትምህርት አስተማረ፣ ቤተክርስቲያንን አቋቋመ፣ የካህን ተንኮልን ጀመረ, አልማ ፩፥፪–፲፮. ቆሪሆር፣ በክርስቶስ፣ በኃጢያት ክፍያው እና በትንቢት መንፈስ ተሳለቀ, አልማ ፴፥፮–፷.